ወልደያ (ኢትዮጵያ)

 
ወልደያ (ኢትዮጵያ)

ወልደያ 

ወልደያ ወይንም ወልዲያ ከደሴ ሰሜን 75 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ከላሊበላ ደግሞ በደቡብ ምስራቅ ያለ በኢትዮጵያ የአማራ ክልል ከተማ ሲሆን በሰሜን ወሎና በወልዲያ ወረዳ ይገኛል። ከኢኮኖሚ አንጻር ለሕንጻ ስራ የሚያገለግል የኖራ ምርት በአካባቢው በትንሹ መካሄዱ በታሪክ ይጠቀሳል።

ታሪክ

ከተማው በታሪካዊ ቦታወች የተከበበ ሲሆን በ1834ዓ.ም. ወልደያን ጎብኝቶ የነበረው ሚስዮኑ ጆዓን ሉዊግ ክራፍ ደጅአዝማች ፋሪስ አሊጋዝ እና ወንድሙ ብሩ አሊጋዝ መምሪያቸውን በዚሁ ቦታ አድርገው እንደነበር ዘግቦት ይግኛል። ሁለቱ ወንድማማቾች በዚያን ወቅት ወረ ይመኑን ለመውጋት ተንቀሳቅሰው እንደነበር ይገልጻል፡፡

በ1880ዎቹ ወልደያ ለዝሆን አደን ተስማሚ ስለነበር በታሪክ ተጠቃሽነት አለው። ከ1880ዎቹ እስከ 1950ዎቹ ወልደያ የየጁ አውራጃ ማዕከል ነበር። በዚህ ወቅት፣ የወልደያ ሆስፒታል በ1929 ዓ.ም በኮንተራክተሩ M.C.M. Pollera ተገነባ። ሆስፒታሉ ሰፊ ቦታ የያዘና ለሰራተኞች ዘመናዊ መኖሪያ ቤት ያለውም ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ሆሰፒታሉ ለከተማው ነዋሪና ለተጎራባች ከተሞች (ላሊበላ፣ አላማጣ፡አፋር፣ ጎንደር) ከፍተኛ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከተማዋ ከፍተኛ የመሰረተ ልማት ግንባታ የሚታይባት ስትሆን በሶስት አቅጣጫ የሚነሱት አውራ መንገዶቹዋም በአስፓልት ኮንክሪት የተሰሩ ናቸው፡፡ የ ፪፬ ሰዓት የ ሀይድሮ ኤሌክትሪክ ፓዎር የምታገኝ ሲሆን በቅርቡ ደግሞ አንድ ዘመናዊ ስታዲዮም ለመስራት የመሰረት ድንጋይ ተቀምጧል፡፡ በከተማዋ ውስጥ ባጃጅ ታክሲዎች በአሁኑ ጊዜ ዋነኞቹ የህዝብ ትራንስፖርት መንገዶች ናቸው፡፡

በ ከመሬት መቀማት ጋር በተነሳ የቀዳማዊ ወያኒ አመጽ ተብሎ በሚታወቀው የ1940 አመጽ ከተማው ላይ በየጁወች ጥቃት ሲደረስ፣ እስር ቤቱ ተከፍቶ እሰረኞች ተለቀቁ። ሆኖም አመጹ የተሳካ አልነበረም  አለም አቀፍ ሃብታም በመሆኑ የሚታወቀው መሀመድ አላሙዲ በ1950ወቹ ለ10 አመት በወልደያ እንዳደገ ይጠቀሳል። ጥቅምት 8-9፣ 1980 ከተማዋ በደርግ አውሮፕላን ብትደበደብም የሞተ ሰው ግን አልተዘገበም።

ከዚህ በተረፈ ወልደያ ላይ የሚገኙት አኖማ ማርያም (በዛፎች ተሸሽጎ ዋሻ ውስጥ የተደበቀ ቤ/ክርስቲያን) እና ወልደያ ገብርኤል ለአካባቢው ታዋቂነትን ይሰጣሉ። ገነተ ማርያምም ከወልደያ ብዙ ሳይርቅ ይገኛል።

የሕዝብ ስብጥር

በ 2007 በተደረገው አጠቃላይ የህዝብ ቆጠራ፣ የከተማዋ የህዝብ ብዛት 46,139 ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 23,000 ወንዶችና 23,139 ሴቶች ናቸው።

አንተ ይፈልጋሉ? አጋራ:

ተዛማጅ ልጥፎች