ትግራይ ክልል

 
ትግራይ ክልል <Tigray Region>
መቐለ
ትግራይ (ክልል 1) ከኢትዮጵያ ዘጠኝ ክልሎች አንዷ ስትሆን በሰሜን-ጫፍ ኢትዮጵያ ትገኛለች። ዋና ከተማዋ መቐለ ነው። ሌሎች ታዋቂ ከተማዎች ውቅሮ፣ ዛላአንበሳ፣ ዓቢ-ዓዲ ፣ዓድዋ፣ ሸራሮ፣ ሑመራ፣ዓዲግራት፣ አክሱም፣ እንዳ-ስላሴ፣ ማይጨው፣ ኮረም እና አላማጣ ናቸው። ኤርትራ፣ ሱዳን፣ የአማራ እና አፋር ክልሎች ያዋስኑዋታል። 50,286 ካሬ ኪ.ሜ. ስትሸፍን የሕዝብ ብዛት 6.2 ሚልዮን ነው። ትግርኛ የክልሉ ዋና ቋንቋ ነው። እምባ ኣላጀ:ፅበት በትግራይ ክልል ከፍተኛ ቦታዎች ናቸው። ትግራይ በኢትዮጵያ ከሚገኙት ክልሎች አንዱ ሲሆን በርካታ ባህላዊ፣ተፈጥራዊ፣ታሪካዊ ሃብት የታደለ ክልል ነው።የሓ ጥንታዊ ቤተ መቅደስ፣ የአክሱም ጥንታዊ ሃወልቶች፣ከ4ኛው እስከ 15ኛው ክ/ዘመን እንደተሰሩ የሚታወቀው ከ120 በላይ የሚሆኑ ከኣለት ድንጋይ ተፈልፍለው የተሰሩ ውቅር ኣብያተክርስትያናትና ገዳማት እንዲሁም ሌሌች በርካታ ታሪካዊና ኣርኪኦሎጂካዊ ስፍራዎች የሚገኙበት ክልል ነው።

ትግራይ ክልል <Tigray Region>

አንተ ይፈልጋሉ? አጋራ:

ተዛማጅ ልጥፎች