አፍሪቃ

 
አፍሪቃ

አፍሪቃ

አፍሪቃ (አፍሪካ) ከዓለም ሁለተኛ ትልቅ አህጉር ነች። ከ869 ሚሊዮን በላይ ህዝብ በዚች አህጉር የሚኖር ሲሆን በጠቅላላ 54 ሀገሮች ይገኛሉ። ከእነዚህም ሀገሮች መሀል ናይጄሪያ በህዝብ ብዛት (127 ሚሊዮን) የመጀመሪያውን ደረጃ ስትይዝ፤ ግብፅና ኢትዮጵያ በ73 ሚሊዮን እና በ72 ሚሊዮን ህዝብ በሁለተኛና በሶስተኛ ደረጃ ይገኛሉ፡፡ በአሁኑ ወቅት የህዝብ ብዛት በከፍተኛ ሁኔታ መጨመር ከሌሎች የፖለቲካና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎች ጋር በመደማመር ድህነትን በማባባስ ደረጃ ትልቅ ሚና ይጫወታል፡፡

ጂዎግራፊና ሕዝብ

ከስድስቱ ዓለማት አንዱ አፍሪካ ነው። አፍሪካ ሰፊ ነው። የዓለምም አራተኛ ክፍል ይሆናል። ከኤውሮጳ የሚለየው በሜዴቲራኒያን ባሕር ነው። ከአሜሪካም በአትላንቲክ ውቅያኖስ ይለያል። ከኒው ዮርክም ቢሆን ወይም ከቦስቶን ከአሜሪካ የሚቀርበው ክፍል ሦስት ሺህ ማይል ይሆናል። ነገር ግን በጊብሮልታር በኩል የሆነ እንደ ሆነ ለኤውሮጳ በጣም ቅርብ ነው።

ከእስያ በኤርትራ ባሕር ይለያያል። የሆነ ሆኖ እስያ ባንድ ወገን ሱዝ ካናል በሚባለው በኩል ከአፍሪካ ጋር ተጋጥሞአል። ሙሴ ሌስፖስ መርከብ እንዲተላለፍ ብሎ አስቆፍሮ ያስከፈተው በዚህ በኩል ነው።

አፍሪካ ከሌላው ዓለም ይልቅ የታወቀው በጣም ትንሽ ነው። ኤውሮጳውያን ደኅና አድርገው አፍሪካን አልመረመሩትም። ከሕዝቡ የሚበልጡት ሻንቅሎች ናቸው። ከነዚህም ብዝዎቹ በነገድ የተለያዩ ናቸው።

ዓየሩ ሙቀት ያለው ስለ ሆነ፣ ለመጠጊያቸው የሚፈልጉት ትንሽ ጎጆና ትንሽ ልብስ ነው። ስለዚህ ቤታቸው የተዋረደ ነው። ቅጠላቅጠሉን ጎጆ ሠርተው በትንሽ ቤት ይኖራሉ። መቸውንም ልብሳቸው አንዲት ቁራጭ ጨርቅ ናት፤ በወገባቸውም ይጠመጥሟታል።

ከሻንቅሎቹ በቀር ደግሞ ሌሎች አያሎች የአፍሪካ ዘሮች አሉ። ከግብፅ ጀምሮ እስከ ሐበሻ ድረስ ያሉት ባላገሮች የጥንት ግብፃውያንነታቸውን ሳይለቁ ከቱርኮችና ከዐረቦች ከሌሎችም የተቀላቀሉ ናቸው።

ሰሐራ የሚባለውን ልክ የሌለውን በረሃና በዙሪያው ያለውን አውራጃ ሁሉ ጨምረው ፈረሶቻቸውንና ግመሎቻቸውን ይዘው ለማሰማራት ወይም ለመዝረፍ ከአንዱ ወዳንዱ የሚዞሩ አረቦች ይዘውታል።

አፍሪካ በመላው ወደ ሥልጣኔ ያልደረሰ ነው ተብሎ ይታሰባል፤ ከሕዝቡ የሚበዙት እስላሞች ናቸው።

በመካከለኛው አፍሪካ አንበሳ፤ ዝሆን፣ አውራሪስ፣ የሜዳ አህያና ሌሎችም አራዊት ይገኙበታል። በደኑ ሁሉ ጦጣና ዝንጀሮ ይንጫጩበታል። በጫካው ውስጥ ዘንዶና ሰጎን ሞልተዋል። በሜዳው አጋዘንና ድኩላ፣ የሜዳ ፍየል ተሰማርተው ይታያሉ። በየወንዙና በየባሕሩ ጎማሬ ይታያል። አዞ በረጋ ውሃ ውስጥ ትኖራለች። አዕዋፍም በየስፍራው ሁሉ ይታያሉ።

አንተ ይፈልጋሉ? አጋራ:

ተዛማጅ ልጥፎች