ፊሊፒንስ | ፊሊፒንስ ካርታዎች | Philippines

 

ፊሊፒንስ | ፊሊፒንስ ካርታዎች | Philippines

ብዙ ልዩ ልዩ ቋንቋዎችና ብሔሮች በፊሊፒንስ ይገኛሉ። ከባህሎቹ ልዩነት የተነሣ፥ በደሴቶቹ ላይ ብዙ ልማዳዊ የሙዚቃ አይነቶች አሉ። ከነዚህ ልዩ ልዩ ሙዚቃዊ ፈሊጦች ጋራ በፊሊፒኖ ባህል የተለያዩ ልማዳዊ ጭፈራ አይነቶች ይሄዳሉ። ለምሳሌ ቲኒክሊንግ፣ ካሪኖሳ እና ሲንግኪል የተባሉ ጭፍራዎች አሉ። በፊሊፒንስ አንዳንድ ጎሣ የተወሳሰበ ብርድ ልብስ ሽመና ስለ መሥራታቸው ዕውቅና አላቸው። ሌሎች ጎሣዎች ጌጣጌጥ ከሉልና ከቀይ መንቁራ ወዘተ. ይሠራሉ። ከሁሉ ቀላል ኑሮ በሩቅ ደን ቦታዎች የሚገኙ ጎሣዎች እስካሁን ድረስ በትንፋሽ የሚነፋ ፒፓ (ፍላጻን ለመውረር) ለማደን እንደ መሣርያ ይጠቅማሉ። በፊሊፒንስ ብቻ የሚማሩ የትግል (ቡጢ) ሥነ ሥርዐቶች ለምሳሌ አሚስ እና ኤስክሪማ ይታወቃሉ።

ጨዋታ በፊሊፒንስ በተለይም ቢሊያርድስ (ከረንቦላን የሚመስል)፣ ቦውሊንግና ሰንጠረዥ (ቼዝ) ይወደዳሉ። እግር ኳስና ቡቅሻ ደግሞ በጣም ይወደዳሉ።

90 ከመቶ የፊሊፒንስ ኗሪዎች የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ናቸው፣ በየከተማውም ስፓኒሾች ከድንጋይ የሠሩ አቡያተ ክርስቲያናት አሁንም አሉ። ሌላ 5 ከመቶ እስላሞች ናቸው፣ የቀሩትም 5 ከመቶ አረመኔ ልማዶች ወይም ሌላ እምነት የሚከተሉ ናቸው።

ብዙ የፊሊፒንስ ኗሪዎች ከቀርከሃ ወይም ዘምባባ እንጨት በተሠራ በቀላል መኖርያ ማደር ይመርጣሉ። ኗሪ ባህሎች ከእስፓንያ፣ ከሜክሲኮ፣ ከፖሊኔዥያ፣ ከአሜሪካ፣ ከቻይና፣ ከሌሎችም እስያዊ አገራት ተጽእኖዎች በመቀላቀሉ፣ እንዲሁም የፊሊፒንስ አበሳሰል ከነዚህ ተጽእኖዎች ሁሉ ይወክላል።

ፊሊፒንስ
ፊሊፒንስ
ፊሊፒንስ
ፊሊፒንስ
ፊሊፒንስ
ፊሊፒንስ
ፊሊፒንስ
ፊሊፒንስ
ፊሊፒንስ
ፊሊፒንስ
ፊሊፒንስ
ፊሊፒንስ

www.megatimes.com.br

አንተ ይፈልጋሉ? አጋራ:

ተዛማጅ ልጥፎች