ድሬዳዋ <Dire Dawa>
ድሬ ዳዋ ከሁለቱ የኢትዮጵያ አስተዳደር አካባቢዎች አንዷ ናት (ሌላዋ አዲስ አበባ ናት)። በ1994 እ.ኤ.አ. የድሬዳዋ ሕዝብ ብዛት 164,851 ነበር።
አቶ መርሻ ናሁሰናይ የድሬዳዋ ቆርቋሪና የመጀመሪያ አስተዳዳሪ (1894 - 1898 እንድ ኢትዮጵያ አቆጣጠር) (1902 - 1906 እንድ አውሮጳ አቆጣጠር)
|
ድሬዳዋ |
|
ጎንደር ከተማ <Gondar>
ጎንደር ቀደም ሲል የጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዛሬ የጎንደር ክፍለ ሐገር እና የጥንትዋ ኢትዮጵያ ዋና ከተማ ነበር። ጎንደር ክፍለህገር በሰባት አውራጅዎች ይከፈላል። እነዚህም አውራጃዎች ከነዋና ከተማቸው የሚከተሉት ናቸው፤ ወገራ አውራጃ ዋና ከተማው ዳባት፣ ሰሜን አውራጃ ዋና ከተማው ደባርቅ፣ ደብረታቦር አውራጃ ዋና ከተማው ደብረታቦር፣ ሊቦ አውራጃ ዋና ከተማው አዲስ ዘመን፣ ጋይት አውራጃ ዋና ከተማው ንፋስ መውጫ፣ ጭልጋ አውራጃ ዋና ከተማው አይክል፣ ጎንደር ዙሪያ አውራጅ ዋና ከተማው ጎንደር ናቸው። የጎንደር እንደ ሰቲት ሁመራ፤ አብደራፊ ወይም ባህረሰላም፣ እንዲሁም መተማ የመሳሰሉ ለም መሬቶች የሚገኙት በጎንደር ክፍለሀገር ነው። ዛሬ በስሜን ጎንደር ዞን በአማራ ክልል ሲገኝ ከጣና ሃይቅ ሰሜን አንገረብ ወንዝ ላይ ከሰሜን ተራራ ወደ ደቡብ ምእራብ ሰፍሮ ይገኛል። በ12°36′ ሰሜን ኬክሮስ እና 37°28′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ነው። አጼ ፋሲለደስ ጎንደርን እንደ ዋና ከተማነት ለመጀመሪያ ጊዜ ይጠቀሙ እንጂ ከዚያ በፊት በአካባቢው ሰወች ይኖሩበት እንደነበር ታሪክ አለ። ሆኖም ግን ከተማው በታሪክ የገነነው አጼ ፋሲለደስ በአሁኑ ፋሲል ግቢ ወይም የነገሥታት ግቢ ውስጥ የፋሲል ግንብን በ1636 ሲያንጽ ነበር።
የማእከላዊ እስታቲስቲክ ባለስልጣን በ1998 ቁጥሩ ጎንደር 194,773 የህዝብ ብዛት ስትይዝ ከነሱም 97,625 ወንዶች ሲሆኑ 97,148 ሴቶች ናችው።
|
ጎንደር ከተማ |
|
ላሊበላ <Lalibela>
ላሊበላ በኢትዮጵያ፣ በአማራ ክልል በቀድሞው የወሎ ክፍለ ሃገር የምትገኝ ከተማ ነች። በ12.04° ሰ 39.04° ምዕ ላይ የምትገኘው የላሊበላ ከተማ ከባህር ጠለል በላይ 2,500 ሜትር ከፍታ ያላት ስትሆን የህዝቡም ብዛት ወደ 11,152 ነው። 1 ላሊበላ ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት ቅዱሳን ከተማዎች መካከል ከአክሱም ቀጥላ በሁለተኛነት ደረጃ የምትገኝ ከተማ ስትሆን፣ ለአብዛኞቹ የክርስትና እምነት ተከታዮች እንደ ዋና የእምነት ማእከል በመሆን ታገለግላለች። የላሊበላ ነዋሪዎች በአብዛኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች ናቸው።
የላሊበላን ከተማ በዋነኛነት ታዋቂ ያረጉዋት ከክ.ል. በኋላ በ13ኛው መቶ ክፍለዘመን እንደ ተሰሩ የሚነገርላቸው 11 አብያተ-ክርስቲያናት ናቸው። በኢትዮጵያ ትውፊት መሰረት እነዚህ አብያተ-ክርስቲያናት በንጉሥ ላሊበላ ዘመን በቅዱሳን መላዕክት እንደተሰሩ የሚታመን ሲሆን ግርሃም ሃንኮክ የተባለው እንግሊዛዊ ፀሃፊ ግን እኤአ በ1993 ዓ.ም ባሳተመውና The Sign and the Seal በተባለው መጽሃፉ አብያተ-ክርስቲያናቱን በማነፁ ሥራ ላይ ቴምፕላርስ የሚባሉት የመስቀል ጦረኞች ተካፍለዋል ሲል አትቷል። እነዚሀ አብያተ-ክርስቲያናት ውስጥ አርባ ትንንሽ ቤተክርስቲያኖች አሉ።
ንጉሡ ላሊበላ የሚለውን ስም ያገኘው፣ ሲወለድ በንቦች ስለተከበበ ነው ይባላል። ላል ማለት ማር ማለት ሲሆን፤ ላሊበላ ማለትም -ላል ይበላል (ማር ይበላል) ማለት አንደሆነ ይነግራል። ውቅር ቤተክርስቲያናቱን ንጉሡ ጠርቦ የስራቸው ከመላእክት እገዛ ጋር እንደሆነ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ይነግራል። በ16ኛው ከፍለ ዘመን አውሮፓዊ ተጓዥ ላሊበላን ተመልክቶ «ያየሁትን ብናግር ማንም እንደኔ ካላየ በፍጹም አያምነኝም» ሲል ተናግሮ ነበር።
በላሊበላ 11 ውቅር ዐብያተ ክርስቲያናት ያሉ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ቤተ ጊዮርጊስ (ባለ መስቀል ቅርፁ) ሲታይ ውሃልኩን የጠበቀ ይመስላል። ቤተ መድሃኔ ዓለም የተባለው ደግሞ ከሁሉም ትልቁ ነው።
|
ላሊበላ |
|
አዲስ ዘመን (ከተማ) <Addis Zemen>
አዲስ ዘመን በደቡብ ጎንደር የሚገኝ ከተማ ሲሆን ከባሕር ዳር ወደ ጎንደር ከተማ በሚጓዘው መንገድ መካከል ይገኛል። በድሮ ስሙ ደብረ አብርሃም ሲባል፣ በአሁኑ ጊዜ የከምከም ወረዳ አስተዳደር ማዕከል በመሆን ያገለግላል።
ከአዲስ ዘመን ከተማ አጠገብ ከሚገኙ ታዋቂ ቦታዎች የደብረ ገላውዲዎስ ገዳም፣ የዋሻ እንድሪያስ፣ ዋሻ ተክለሃይማኖት አብያተ ክርስቲያናት እና አስባ ተራራዎች ይገኛሉ። ታሪካዊው ጉዛራም እንዲሁ በቅርብ ይገኛል። ደብረ ገላውዲዎስ በዓፄ ገላውዲዎስ ዘመን በነበረ ቅዱስ ሰው የተመሰረተ ሲሆን በቆዩ የግድግዳ ምስሎቹና ከ16ኛው ክፍለ ዘመን በሚመነጩ የወይራ ዛፎቹ ይታወቃል። በኋላ በ1572ዓ.ም. አንድ የኦሮሞ ነገድ በንጉሱ በዓፄ ሱሰንዮስ ላይ ዘመቻ ሲከፍት የዓፄ ሠርፀ ድንግል እናት ወደዚህ ቦት ደብረ አብርሃም መጥታ እንደተጠለለች ታሪክ ይዘግባል[1]።
አዲስ ዘመን፣ ከ1956-1972 ዓ.ም የሊቦ አውራጃ ማዕከል በመሆንም አገልግሏል። በ1958 በተደረገ የህዝብ ቆጠራ አዲስ ዘመን ውስጥ 4400 ሰዎች የነበሩ ሲሆን፣ ከደብረ ማርቆስ የሚመጣው የስልክ አገልግሎት እዚህ ከተማ ደርሶ ነበር። በአጠቃላይ 3 ቢሮዎች እና 2 ግለሰቦች የስልክ አገልግሎት ተጠቃሚ ነበሩ።
|
አዲስ ዘመን (ከተማ) |
|
አክሱም <Axum>
አክሱም በሰሜን ኢትዮጵያ በትግራይ ክ/ሃገር ከአድዋ ተራራዎች አጠገብ የምትገኝ ከተማ ነች። በክርስቶስ ልደት በፊት ተመስርቶ የነበረው የአክሱም ስርወ መንግስት ማእከል ነበረች። የአክሱም ስርወ መንግስት በ12ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አካባቢ እየተዳከመ ሲመጣ የማእከላዊው መንግስት ወደ ደቡብ ተንቀሳቀሰ። ሰባ አምስት በመቶ የሚሆነው የከተማው ነዋሪ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታይ ነው። የተቀሩት ነዋሪዎች የሱኒ እስልምና ተከታዮች ናቸው። ባላቸው ታሪካዊ ተፈላጊነት ከተማ ውስጥ የሚገኙት የአክሱም ስርወ መንግስት ቅሪቶች UNESCO በ1980 የአለም ቅርስ ቦታ ተብለው ተሰይመዋል። አክሱም በኢትዮጵያ የ ትግራይ ክልል ከተማ ሲሆን በማዕከላዊ ዞንና በላዕላይ ማይጨው ወረዳ ይገኛል። በ1998 ማዕከላዊ የስታትስቲክስ ባለስልጣን እንደተመነው የ47,320 ሰው መኖሪያ ሲሆን እነሱም 23,542 ወንዶችና 23,778 ሴቶች ይገኙበታል።
በሌላ ገለልተኛ ትምና ደግሞ የ41,197 ሰው መኖሪያ ተደርጎ ተገምቷል። የከተማው አቀማመጥ በ14°07′ ሰሜን ኬክሮስ እና 38°44′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ነው።
|
አክሱም |
|
አዲግራት <Adigrat>
አዲግራት በኢትዮጵያ የትግራይ ክልል ከተማ ሲሆን በምስራቃዊ ዞንና በጋንታ አፈሹም ወረዳ ይገኛል። በ1998 ማዕከላዊ የስታትስቲክስ ባለስልጣን እንደተመነው የ65,237 ሰው መኖሪያ ሲሆን ከነሱም 32,586 ወንዶችና 32,651 ሴቶች ይገኙበታል። አዲግራት ከመቀለ በሰሜን በኩልና ከሰናፌ በደቡብ በኩል ትገኛለች።
በሌላ ገለልተኛ ትምና ደግሞ የ84,769 ሰው መኖሪያ ተደርጎ ተገምቷል። የከተማው አቀማመጥ በ14°16′ ሰሜን ኬክሮስ እና 39°27′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ነው።
|
አዲግራት |
|
መቀሌ <Mek'ele>
መቀሌ (ትግርኛ፦ መቐለ) የትግራይ ክልል ዋና ከተማ ናት። ከአዲስ አበባ 783 ኪ.ሜ. ወደ ሰሜን ትገኛለች። ከ150,000 አስከ 250,000 የሚገመት የሕዝብ ብዛት ስላላት ከሰሜን ኢትዮጵያ ትልቁ ከተማ ያደርጋታል። መቀሌ ለዮሐንስ ፬ኛ ዋና ከተማ በመሆን በ19ኛው ክፈለ ዘመን ነው የተመሠረተችው። መቀሌ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙት ከተሞች በ ንግድና ትምህርታዊ ማዕከላዊነትዋ ትታወቃለች። እጅግ ታላቅና ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ በታላቁ አፍሪካዊ ጄነራል ራስ አሉላ አባነጋ የተሰየመ አየረ ማረፊያ አላት። በተጨማሪም እንደነ መስፍን ኢንዱስትርያል፣ መሰቦ ሲሚንቶ፤ታላላቅ ፋብሪካዎችና ዩኒቨርሲቲ መቐለም በከተማዋ ይገኛሉ።
|
መቀሌ |
|
ማይጨው <Maychew>
ማይጨው (ትግርኛ ማይጭው "የጨው ውኃ") በስሜን ኢትዮጵያ ያለች መንደር ናት። ከደሴ 190 ኪሎ ሜትር ወደ ስሜን በአዲስ አበባ-አስመራ መንገድ በትግራይ ክልል ደቡባዊ ክፍል ስትገኝ ኬክሮሷና ኬንትሮሷ 12°47′ ሰሜን ኬክሮስ እና 39°32′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ከፍታዋም 2,479 ሜትር ነው።
በ1997 ዓ.ም. ከማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ በቀረበው ቁጥር መሠረት የማይጨው ጠቅላላ ሕዝብ ቁጥር 34,379 ሰዎች እንደ ነበር ይገመታል። ከነዚህም 16,702 ወንዶችና 17,222 ሴቶች ነበሩ። በ1984 ብሄራዊ ቆጠራ ግን 19,757 ኗሪዎች ነበሩ።
በማይጨው አካባቢ ግጥሚያ በመጋቢት 22 ቀን 1928 ዓ.ም. በጣልያ ጦርነት ጊዜ የፋሺስት ሃያላት በመሳርያዎች ምክንያት ድል አድርገው ወደ አዲስ አበባ ቀረቡ።
|
ማይጨው |
|
ጎባ <Goba>
ጎባ በኢትዮጵያ የኦሮሚያ ክልል ከተማ ሲሆን በባሌ ዞንና በጎባ ወረዳ ይገኛል። በ1998 ማዕከላዊ የስታትስቲክስ ባለስልጣን እንደተመነው የ50,650 ሰው መኖሪያ ሲሆን ከነሱም 24,256 ወንዶችና 26,394 ሴቶች ይገኙበታል።
በሌላ ገለልተኛ ትምና ደግሞ የ34,868 ሰው መኖሪያ ተደርጎ ተገምቷል። የከተማው አቀማመጥ በ7°00′ ሰሜን ኬክሮስ እና 39°58′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ነው።
|
ጎባ
|
|
አዳማ <Adama>
ኣዳማ በአማርኛ ናዝሬት በኦሮሚያ ክልል ለኦሮሚያ በዋና ከተማነት የሚያገለግል የኢትዮጵያ ከተማ ነው። በምስራቅ ሸዋ ዞን በላቲቱድና ሎንጂቱድ 8.55° N 39.27° E ላይ ከአዲስ አበባ ወደ ደቡብ ምዕራብ 100 ኪሎመትር ላይ ይገኛል።
በማዕከላዊ ስታቲስቲስ ባለስልጣን ትመና የአዳማ ከትማ የ228,628 ሰው መኖሪያ ሲሆን እነሱም 114,255 ወንዶችና 114,368 ሴቶች ናቸው። ሌሎች ትመናዎችም አዳማ ከ200,000 ህዝብ በላይ መያዙን ያዘግባሉ። በ1986 የሕዝብ ቆጠራ አዳማ የ127,842 መኖሪያ ነበር።
አዳማ በትራንስፖርት ማእከልነት የታወቀ ከተማ ነው። ከተማው በአዲስ አበባና በድሬዳዋ መንገድ ላይ ይገኛል። አዲስ አበባ ጅቡቲና አሰብ (ከኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት በፊት ኢትዮጵያ አሰብን ስትጠቀም) የሚመላለሱ ቁጥራችው ከፍ ያሉ የጭነት መኪኖች የሚያልፉት በአዳማ ነው። ከአዲስ አበባ ወደ ጅቡቲ የሚሄደው ምድር ባቡርም አዳማን ያቋርጣል።
|
አዳማ
|
|
አድዋ <Adwa>
ዓድዋ በኢትዮጵያ የትግራይ ክልል ከተማ ሲሆን በማዕከላዊ ዞንና በዓድዋ ወረዳ ይገኛል። በ1998 ማዕከላዊ የስታትስቲክስ ባለስልጣን እንደተመነው የ42,672 ሰው መኖሪያ ሲሆን ከነሱም 20,774 ወንዶችና 21,898 ሴቶች ይገኙበታል።
|
አድዋ |
|
አጋሮ <Agaro>
አጋሮ በኢትዮጵያ የኦሮሚያ ክልል ከተማ ሲሆን በጅማ ዞንና በጎማ ወረዳ ይገኛል። በ1998 ማዕከላዊ የስታትስቲክስ ባለስልጣን እንደተመነው የ41,616 ሰው መኖሪያ ሲሆን ከነሱም 21,549 ወንዶችና 20,067 ሴቶች ይገኙበታል። እስከ 1878 ዓ.ም. ድረስ የጎማ መንግሥት ዋና ከተማ ነበረ።
በሌላ ገለልተኛ ትምና ደግሞ የ28,668 ሰው መኖሪያ ተደርጎ ተገምቷል። የከተማው አቀማመጥ በ7°5′ ሰሜን ኬክሮስ እና 36°39′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ነው።
|
አጋሮ |
|
አምቦ <Ambo>
አምቦ በኢትዮጵያ የኦሮሚያ ክልል ከተማ ሲሆን በምዕራብ ሸዋ ዞን ና በአምቦ ወረዳ ይገኛል። በ1998 ማዕከላዊ የስታትስቲክስ ባለስልጣን እንደተመነው የ49,421 ሰው መኖሪያ ሲሆን ከነሱም 24,671 ወንዶችና 2475 ሴቶች ይገኙበታል።
በሌላ ገለልተኛ ትምና ደግሞ የ43,029 ሰው መኖሪያ ተደርጎ ተገምቷል። የከተማው አቀማመጥ በ11°28′ ሰሜን ኬክሮስ እና 36°12′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ነው።
|
አርባ ምንጭ <Arba Minch>
አርባ ምንጭ በኢትዮጵያ የደቡብ ብሄር ብሄረስቦችና ሕዝቦች ክልል ከተማ ሲሆን በጋሞጎፋ ዞን (ቀድሞ ሰሜን ኦሞ ዞን)ና በአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ይገኛል። በ1998 ማዕከላዊ የስታትስቲክስ ባለስልጣን እንደተመነው የ72,507 ሰው መኖሪያ ሲሆን ከነሱም 36,296 ወንዶችና 36,211 ሴቶች ይገኙበታል።
በሌላ ገለልተኛ ትምና ደግሞ የ68,816 ሰው መኖሪያ ተደርጎ ተገምቷል። የከተማው አቀማመጥ በ6°2′ ሰሜን ኬክሮስ እና 37°33′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ነው።
|
አሰላ <Asella>
አሰላ የአርሲ ክፍለሀገር ዋና ከተማ ነው። ተራራማ ቦታ ላይ የሚገኝ ሲሆን የአየር ንብረቱ ደጋማ ነው። ከአዲስ አበባ ደቡብ ምስራቅ 175 ኪ.ሜ ያህል ይርቃል። አሰላ በ 7°57'ሰሜን ኬክሮስ እና በ 39°7'ምስራቅ ኬንትሮስ ይገኛል። የመሬቱ ከፍታ 2430 ሜትር ከ.ጠ.በ. ሲሆን በስሙ የተመዘገበ የአየር ማረፊያ አለው ።
|
አሶሳ <Asosa>
አሶሳ (የቀድሞ ስሙ አቆልዲ) የቤንሻንጉል-ጉምዝ ክልል ዋና ከተማ ናት። በ1994 እ.ኤ.አ. የሕዝብ ብዛቱ 11,749 ሰዎች ሲሆን በ1997 ቆጠራ መሠረት 20,226 ሰዎች ነው።
ከኮንጎ የመጣ የቤልጅግ ሠራዊት በመጋቢት 2 ቀን 1933 ዓ.ም. የጣልያንን ሠራዊት አሸንፎት 1500 ወታደሮች ማርኮ አሶሳን ያዘ።
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ጦርነት ግዜ ኦነግ በወያኔ እርዳታ አሶሳን ከደርግ ሃያላት ያዘ።
|
አዋሳ <Awasa>
አዋሳ ከአዋሳ ሃይቅ በታላቁ ሪፍት ቫሌ/ስምጥ ሸለቆ ላይ የሚገኝ ከተማ ነው። የደቡብ ሕዝቦች ክልል ዋና ከተማ ስተሆን በሲዳማ ዞን ተገኛለች። የአዲስ አበባ-ናይሮቢ መንገድ ላይ በላቲቱደና ሎንጁቱድ 7°3′ ሰሜን ኬክሮስ እና 38°28′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ናት። አዋሳ በውበትዋና በትልቅነትዋ ባሁኑ ጊዜ ታላቅ የቱሪስት መስህብ ያላት ነች።
በማዕከአዊ ስታቲስቲክ ባለስልጣን ትመና የ119,623 ሰው መኖሪያ ስትሆን ከነሱም 60,378 ወንዶች 59,245 ሴቶች ሆነው ተተምነዋል። አዋሳ የቀድሞ ሲዳሞ ክፍለ ሓገር ዋና ከተማ የነበረች የደቡብ ዩኒቨርሲቲ፥ የአንድ ኤርፖርትና የሰፊ ገበያ ማዕከል ናት። አዋሳ ከ1998 ዓ.ም. ጀምሮ ሃዋሳ በመባል የታወቃል። ይህን ተመርክዞ የደቡብ ዩኒቨርሲቲ ሃዋሳ በመባል ስሙ ተቀይሮአል።
የሃዋሳ ከተማ በአሁን ሰዓት በከፍተኛ ደረጃ እያደገች ያለች ከተማ ሰትሆን ወደ 600,000 ነዋሪ እንደሚገኝባት ይገመታል። ከተማዋን በሰሜን ኦሮምያ በደቡብ ዲላ በምዕራብ ከምባታ በ ምስራቅ አለታ ወንዶ ያዋስኑዋታል።
|
አላማጣ <Alamata>
አላማጣ በኢትዮጵያ የትግራይ ክልል ከተማ ሲሆን በደቡባዊ ዞንና በአላማጣ ወረዳ ይገኛል። በ1998 ማዕከላዊ የስታትስቲክስ ባለስልጣን እንደተመነው የ45,632 ሰው መኖሪያ ሲሆን ከነሱም 22,712 ወንዶችና 22,920 ሴቶች ይገኙበታል።[1]
በሌላ ገለልተኛ ትምና ደግሞ የ48,262 ሰው መኖሪያ ተደርጎ ተገምቷል። የከተማው አቀማመጥ በ12°24′ ሰሜን ኬክሮስ እና 39°33′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ነው።
በአላማጣ አኻባቢ የሚገኘው መሬት በጣም ለም ሲሆን ለእርሻም ተሲማሚ ነው።
|
ባሕር-ዳር <Bahir Dar>
ባሕር-ዳር በድሮ ስሙ ባሕር ዳር ጊዮርጊስ በሰሜን-ምዕራብ ኢትዮጵያ የምትገኝ ከተማ ስትሆን የአማራ ክልል ዋና ከተማ ናት። ከተማዋ በቀድሞው ጎጃም ክፍለ ሓገር ውስጥ ከጣና ሐይቅ ደቡባዊ ጫፍ ላይ ተቀምጣ ስትገኝ ባህር ዳር እንደ መቀሌና ደሴ የወረዳ ደረጃ ያላት ስፔሻል(ልዩ) ዞን ናት። በማዕከላዊ ስታትስቲክ ትመና የ167,261 ህዝብ ከነሱም መሃከል የ86,355 ወንዶችና የ80,906 ሴቶች መኖሪያ ከተማ ናት። 1700 ሜትር ከባሕር ወለል በላይ ትገኛለች።
መገኛ
ባሕር-ዳር ከአዲስ አበባ 565 ኪ.ሜ ወደ ሰሜን-ሰሜን ምዕራብ ትገኛለች። ባህር ዳር ከጢስ አባይ በ30 ኪሎመተር ስለምትርቅ ለጎብኚዎች አመቺ ቦታ ላይ ናት። ባህር ዳር የአንድ የአስፋልት ንጣፍ ያለው ኤርፖርት የሰፊ ገበያና የተለያዩ የመዝናኛ ቦታዎች እና ታሪካዊ እና ጥንታዊ ግዳማት መግኛ ቦታ ናት።
ባሕርዳር ከተማ የምትገኘዉ በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ ክፍል፣ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት፣ በምዕራብ ጎጃም ዞን፣ ከአዲስ አበባ በ 565 ኪሜ ርቀት ላይ ነው፡፡ አስትሮኖሚያዊ መገኛ ቦታዋ በ 11º 38’ በሰሜን ላቲቲውድ እና በ37º15’ ምስራቅ ሎንግቲውድ ነው፡፡
በአፈ ታሪክ እንደሚነገረው የባሕር-ዳር ስያሜን ያወጡት አፄ ሠርጸ ድንግል ሲሆኑ እሳቸውም ይሕን ታቦት የት እናስቀምጥ ተብለው በተጠየቁ ጊዜ "ከባሕሩ-ዳር" አድርጉ የተባሉ ሰወች ለመንደሩ ባሕር-ዳር ብለው ስያሜ አወጡለት ይባላል።
ባሕርዳር ከተማ የተቆረቆረችው በ1915 ዓ.ም ነው ፡፡ ባሕርዳር በክልሉ ከሚገኙ የሪፎርም ከተሞች አንድዋ ስትሆን፤ የከተማ አስተዳደር፣ 3 ሜትሮፖሊታን ክ/ከተማዎች፣ የከተማ አገልግሎት ጽ/ቤት፣ 9 የከተማ ቀበሌዎችና 4 የገጠር ቀበሌዎች አሏት፡፡ ከተማዋ በ1998 ዓ.ም የተቀናጀ ልማት ፕላን አላት፡፡
የተቆረቆረችበትን ዓመት፣ የቆረቆሩትን ቀደምት ሠዎች፣ የሠፈሮችን ስሞች፣ ለባሕር ዳር የተገጠሙትና የተዘፈኑ ታሪካዊ ግጥሞችና ስነ ቃሎች፣ ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከጎጆ ቤት ወደ አሁኑ ይዞታው አመጣጥ (ባሕር ዳርን ስናስብ ጊዮርጊስን ሚካኤልን እና ገበያውን ከገበያው አካባቢ የነበረውን ፍርድ ቤት ነጣጥሎ ማየት አይቻልም የሚል አስተያየት ስላለ ነው)፣ ባሕር ዳር እንደባሕር ዳርነቱ ከመቆርቆሩ በፊት በሚካኤል እና በሽመምብጥ ሠፈር አካባቢ ስለነበረው አሰፋፈር፣ ስለማዘጋጃቤቱ፣ ስለ አውቶቡስ ተራው፣ ስለ ድባነቄ ተራራ፣ እና ስለ መሳሉት፣ ስለፖሊቴክኒክ፣ ስለዓባይ ወንዝና ድልድዩ፣ ስለዓባይ ወንዝና ስለጣና ሐይቅ መገናኛ እና ስለሌሎችም ቁልፍ ነገሮችን ማቅረብ የሚችሉ አፈታሪኮች አሉ።
|
ደብረ ዘይት <Bishoftu>
ደብረ ዘይት በኢትዮጵያ የኦሮሚያ ክልል ከተማ ሲሆን በምስራቅ ሸዋ ዞንና በአድአ ጨዘላ ወረዳ ይገኛል። በ1998 ማዕከላዊ የስታትስቲክስ ባለስልጣን እንደተመነው የ131,159 ሰው መኖሪያ ሲሆን ከነሱም 64,642 ወንዶችና 66,517 ሴቶች ይገኙበታል።
በሌላ ገለልተኛ ትምና ደግሞ የ104,537 ሰው መኖሪያ ተደርጎ ተገምቷል። የከተማው አቀማመጥ በ8°45′ ሰሜን ኬክሮስ እና 38°59′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ነው።
|
ቦንጋ <Bonga>
ቦንጋ የኢትዮጵያ ከተማ ነው።
|
ደብረ ብርሃን <Debre Berhan>
ደብረ ብርሃን በሸዋ ክፍለ ሀገር የተጉለትና ቡልጋ አውራጃ ዋና ከተማ ናት። ከተማዋ የሰሜን ሸዋ ዞን (አውራጃ) አስተዳደር ርዕሰ ከተማ ከመሆኗ ባሻገር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስም ዋና ጽሕፈት ቤት እዚሁ ይገኛል።
በ፲፱፻፺፰ ዓ/ም ማዕከላዊ የስታትስቲክስ ባለስልጣን እንደተመነው ደብረ ብርሃን ከተማ የ፷፯ ሺህ ፪፻፵፫ ሰው መኖሪያ ስትሆን ከነሱም ፴፬ ሺህ ፶፭ ወንዶችና ፴፫ ሺህ ፻፹፰ ሴቶች ይገኙባታል ይላል።
በሌላ ገለልተኛ የግምት ትመና ደግሞ ከተማዋ የ፶፯ ሺህ ፯፻፹ ሕዝብ መኖሪያ እንደሆነች ተገምቷል። የከተማዋ አቀማመጥ በ9°41′ ሰሜን ኬክሮስ እና 39°32′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ነው።
ደብረ ብርሃን ከአዲስ አበባ ፻፴ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በደሴ መስመር ላይ የምትገኝ ስሆን ፱ የአስተዳደር ቀበሌዎችም አሏት። የአየር ንብረቷ ደጋማ ነው። የተቆረቆረችውና ስያሜዋን ያገኘችው ደግሞ በ፲፬፻፵፮ ዓ/ም አካባቢ በዓፄ ዘርአ ያዕቆብ (፲፬፻፴፬-፲፬፻፷፰) ነበር። ከተማዋ ድሮ የንጉሡ የግራ በአልቴሃት (ግራ በአልቴሃት ከንጉሡ ሦሥት ሚስቶች የአንደኛዋ የክብር ስም ነው) ርስት ነበረች። በ፲፬፻፵ዎቹ መጀመሪያ አጤው ከእንደግብጣን ወጨጫ ተራራ ማለትም ከአዲስ አበባ በስተምዕራብ ከነበረው ያባታቸው አጤ ዳዊት መናገሻ ሥፍራ ተነስተው ሲጓዙ በአካባቢው ውበት ስለተደሰቱ የድንኳን ከተማቸውን ከተሙባት። በኋላም ቤተ መንግሥት አሳንፀውና ባለወርቅ ጉልላት የነበረውን የሥላሴ ቤተ ክርስቲያን አሰርተው ቆረቆሯት። "ተአምረ ማርያም" የተሰኘ የጥንት ድርሳን የከተማዋን ስያሜ ከአንድ ተአምራዊ ሁነት ጋር አያይዞ ይገልፀዋል። በ፲፬፻፵፮ ዓ/ም በክርስትና ሃይማኖት ካህናትና በጥቂት የሃይማኖቱ ተከራካሪዎች መካከል ክርክር ይነሳል። ንጉሡና የካህናቱ አለቆች በተገኙበት አንድ ዕለት በጉባዔ ክርክሩ ተካሄደ። በመጨረሻም «እስጢፋኖሳውያን» በሚል መጠሪያ የሚታወቁት ተከራካሪዎች አቋማቸውን እንዲያስተካክሉ ተጠይቀው አሻፈረን በማለታቸው ከፍተኛ ቅጣት ይደርስባቸዋል። ይህ በሆነ በ፴፰ኛው ቀን በመጋቢት ፲ ቀን 1446|፲፬፻፵፮ ዓ/ም ረዘም ላለ ጊዜ / ምናልባትም ለቀናት/ የቆየ ቦግ ያለ ብርሃን ከሰማይ ይወርዳል። የብርሃኑ መውረድ ለእስጢፋኖሳውያን ስህተተኛነት ለካህናቱ ደግሞ ትክክለኛነት ምስክር ነው በሚል ተተርጉሟል። ስለዚህ ብርሃን መውረድ የንጉሡ ዜና መዋዕልም ያትታል። በዚህ ሳቢያ ንጉሡ የሥፍራውን ስም ደብረ ብርሃን /የብርሃን አምባ/ በማለት ሰይመውታል።
ዓፄ ዘርአ ያዕቆብ ከንግሥና ዘመናቸው ፲፬ ዓመታት የሚሆነውን በደብረ ብርሃን ከተማ እንዳሳለፉና አብዛኛዎቹን የሃይማኖትና የፍልስፍና ድርሰቶቻቸውን የፃፉት በዚሁ ከተማ መሆኑ ይነገራል። በዘመኑም ደብረ ብርሃን ከፍተኛ የትምህርት ማዕከል የነበረች ሲሆን በንጉሡ ትእዛዝ በርካታ የሃይማኖት መፃሕፍት የትርጉም ሥራ ተከናውኖባታል።
በዓፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት የኣዲስ ኣበባ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሲጣበቡ ለሸዋ ጠቅላይ ግዛት ተማሪዎች እንዲያገልግል ኃይለ ማርያም ማሞ ፪ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ደብረ ብርሃን ተሠራ። ለመጀሪያዎቹ ስድስት ዓመታት ለተማሪዎቹም መጀመሪያ በየወሩ ፳ ብር በኋላም ፲፭ ብር እየተፈልላቸው ነበር የተማሩት። ከምሩቃኖቹም መካከል ዶ/ር ኣበራ ሞላ ይገኙበታል።
|
ደብረ ማርቆስ <Debre Marqos>
ደብረ ማርቆስ በኢትዮጵያ በአማራ ብሔራዊ ክልል የሚገኝ ሲሆን የምስራቅ ጎጃም ዞን ዋና ከተማ ናት። ከተማዋ በውስጧ የደብረ ማርቆስ ወረዳ ይዛ ትገኛለች። በ1998 ማዕከላዊ የስታትስቲክስ ባለስልጣን እንደተመነው የ85,597 ሰው መኖሪያ ሲሆን ከነሱም 43,229 ወንዶችና 42,368 ሴቶች ይገኙበታል። መገኛ
የደብረማርቆስ ከተማ የምትገኘው በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምስራቅ ጎጃም ከአዲስ አበባ በ 300 ኪ.ሜ ከባህር ዳር ደግሞ 265 ኪ.ሜ፣ በ 37021’ ሰሜን ላቲቲውድ እና 37º 43’ ምስራቅ ሎንግቲውድ ነው፡፡
አመሰራረት
ደብረማረቆስ ከተማ የጎጃም ገዥ በነበሩት ደጃዝማቸ ተድላ ጓሉ በ1845 ዓም የተቆረቆረች ሲሆን የከተማዋም መጠሪያ መንቆረር ይባል ነበር፡፡ በ 1872 ዓም ወደ ሥልጣን የመጡት ንጉስ ተክለሃይማኖት ካሁኑ ቅዱስ ማርቆስ ቤተክርስቲያን መመስረት ጋር ተያይዞ የከተማዋ ስያሜ መንቆረር መባሉ ቀርቶ ደብረ ማረቆስ እንዲሆን አዋጅ በማስነገራቸው የከተማዋ መጠሪያ ሊሆን በቃ፡፡ ደብረማርቆሰ በክልሉ ከሚገኙ የሪፎርም ከተሞች አንዷ ስትሆን ከተማዋ በስሯ 6 ቀበሌዎችና ማዘጋጃ ቤት ያሉት የከተማ አስተዳደር አላት፡፡ በ2002 ዓ.ም የተዘጋጀ የተቀናጀ ልማት ፕላን አላት፡፡ [1]
በሌላ ገለልተኛ ትምና ደግሞ የ60,796 ሰው መኖሪያ ተደርጎ ተገምቷል:: የከተማው አቀማመጥ በ10°20′ ሰሜን ኬክሮስ እና 37°43′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ነው። ደብረ ማርቆስ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የመሰረተ ልማት እየተሟላላት ነው። ከተማዋ አዲስ ድረገጽ ከፍታለች።
|
ደብረ ታቦር (ከተማ) <Debre Tabor>
ደብረ ታቦር (በሌላ ስሟ ሰማራ ) በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ከጣና ሓይቅ ሰሜናዊ ምስራቅ 50 ኪሎ ሜተር ርቃ የምተገኝ በተራሮች የተከበበች ከተማ ናት። በከተማይቱ ዙሪያ 48 ምንጮች መኖራቸው ለከተማይቱ እድገት ከፍትኛ አስተዋጾ ቢያደርጉም በ20ኛው ክፍለ ዘመን የባህር ዛፍ ተክል በከተማይቱ መሰራጨት ምንጮቹ እንዲደርቁ አድርጓል። የደብረታቦርን መሰረት የጣለው የ14ኛ ክፍለዘመን ንጉስ አጼ ሰይፈ አርድ (1344-1372) ነበር። በዚህ ንጉስ ዘመን ጥንታዊው የታቦር እየሱስ ቤ/ክርስቲያን በደብረ ታቦር ተራራ ላይ ታነጸ። ቤተ ክርስቲያኑ በንዲህ ከቆየ በኋላ በ18ኛ ክፍለ ዘመን መገባደጃ ላይ በራስ ጉግሳ ሙርሳ እንደገና ታድሶ ተሰራ። ራስ ጉግሳ የደበረታቦር ከተማን በዚያው ስም ከሚታወቀው ተራራ ሰሜን ትይዩ እንደቆረቆረ ይነገራል።[1] ራሱና ልጆቹ ለከተማይቱ መቋቋም አስተዋጾ ቢያበረክቱም ከተማይቱ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ በሰፊው የምትጠቀሰው አጼ ቴወድሮስ እና ከዚያም ቀጥሎ አጼ ዮሐንስ ፬ኛ እንደ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ በማገልገል ነው። ከሞላ ጎደል ደብረ ታቦር(ሳማራ) የ19ኛው ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያ ዋና ከተማ በመሆን አገልግላለች። ተጭነው ስለተለያዩ የከተማይቱ ክፍሎች መርጃ የሚያገኙበት ካርታ እዚህ ይገኛል።
|
ደብረ ወርቅ <Debre Werq>
ደብረ ወርቅ በምስራቅ ጎጃም፣ እናርጅ እናውጋ ወረዳ ውስጥ ከሚገኙት ሁለት ከተሞች ታላቁ ነው። በከተማው ዳርቻ የሚገኘው የደብረ ወርቅ ማርያም ቤተክርስቲያን በአካባቢው ዘንድ ታዋቂነትን ያስገኘዋል።
ደብረወርቅ ለመጀመሪያ ጊዜ በታሪክ ተመዝግቦ የሚገኘው ፣ ከዚሁ አካባቢ የፈለሱ ተሳላሚዎች ፋዩም፣ግብጽ ውስጥ ዳር አል አብያድ በተሰኘ ገዳም ስማቸውንና የመጡበትን ቦታ በቀለም ስላስመዘገቡ ነው ። ይሄውም በ ሰኔ 8፣ 222 ዓመተ ምህረት ( ሰኔ8፣ 1038 ዓ.ም.) መሆኑ ነው። ዓፄ በእደ ማርያም ሕዳር 12፣ 1470 በዚሁ ቦታ በሞት እንዳረፉ ይጠቀሳል።
|
ዲላ <Dila>
ዲላ በኢትዮጵያ የደቡብ ብሄር ብሄረስቦችና ሕዝቦች ክልል ከተማ ሲሆን በጌዴዎ ዞንና በወናጎ ወረዳ ይገኛል። በ1998 ማዕከላዊ የስታትስቲክስ ባለስልጣን እንደተመነው የ61,114 ሰው መኖሪያ ሲሆን ከነሱም 31,329 ወንዶችና 29,785 ሴቶች ይገኙበታል።[1] ወጣት ቶፊቅ ጀማል የዲላ ከተማ ነዋሪ ሲሆን በአሁኑ ስእት ሃራማያ ዩኒቨርስቲ ኮምፒዩተር ስይንስ ተመራቂ ተማሪ ነው።ይህ ገለስብ ዲላ ከተማን ለሃያ ኦመታት ስእስትዳዲር ኖሮኦል።
በሌላ ገለልተኛ ትምና ደግሞ የ47,214 ሰው መኖሪያ ተደርጎ ተገምቷል። የከተማው አቀማመጥ በ6°25′ ሰሜን ኬክሮስ እና 38°19′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ነው።
|
ፍኖተ ሰላም <Finote Selam>
የፍኖተሰላም ከተማ የምትገኘው በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምዕራብ ጎጃም ዞን ጃቢጠህናን ወረዳ ከአዲስ አበባ በ 387 ኪ.ሜ ከክልሉ ዋና ከተማ ባህርዳር ደግሞ 176 ኪ.ሜ ላይ ነው፡፡ አስትሮኖሚያዊ መገኛ ቦታዋም በ10º 41’ ሰሜን ላቲቲውድ እና 37º 16’ ምስራቅ ሎንግቲውድ ነው፡:1 ፍኖተ ሰላም (ፍ/ሰላም) በኢትዮጵያ ውስጥ በጎጃም እምብርት ላይ የምትገኝ ከተማ ናት።
አመሰራረት
ፍኖተሰላም ከተማ የተቆረቆረችው በ 1933 ዓም ነው፡፡ፍኖተሰላም በክልሉ ከሚገኙ የሪፎርም ከተሞች ስትሆን፣ የከተማ አስተዳደር፣ ማዘጋጃ ቤት፣ 3 የከተማና 2 የገጠር ቀበሌዎች አላት፡፡ በ2003 ዓ.ም የተዘጋጀ መዋቅራዊ ፕላንም አላት፡፡ ፍኖተ ሰላም ማለት መልካም መንገድ ወይም ጉዞ እንደማለት ሲሆን ይህንንም ስም ያወጡላት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ እንደሆኑ ይነገራል። ጃንሆይ ከጣሊያን ጦርነት በኋዋላ ከስደት ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱ አሁን ፍኖተ ሰላም ያለችበት ቦታ ላይ ከአጃቢዎቻቸው ጋር እረፍት ያደርጋሉ። እስከዚያን ጊዜ ድረስ ያደረጉት ጉዞም በሰላም የተሞላ ስለነበር ያንን ቦታ ፍኖተ ሰላም ብለው ሰየሙት። ከከተማዋ ወጣ ብሎ የሚገኝ አንድ የዋንዛ ዛፍ ይገኛል። ይህንንም የዋንዛ ዛፍ የተከሉት ንጉሱ ስለነበሩ እስካሁን ድረስ የአባ ንጉስ ዋንዛ እየተባለ ይጠራል።
ፍኖተ ሰላም በብዙ ነገር ትታወቃለች። በአካባቢው ያሉ ገበሬዎች ጤፍ፣ በቆሎ፣ ዳጉሳ፣ ኑግ፣ በርበሬ እና ሌሎችንም የእህል አይነቶች ያበቅላሉ። በፍራፍሬ ሎሚ፣ ብርቱካን፣ ፓፓዬ እንደልብ ይገኛል። በጣም ጥራት ያለው ቡና የሚገኝባት አገር ናት - ፍ/ሰላም። የባከል ቡና በጣዕሙ ይታወቃል። ከከተማው ወጣ ብሎ የገራይ የውሃ ግድብ ስለሚገኝ በተለይ በፆም ጊዜ እጅ የሚያስቆረጥም አሳ ይገኛል። ፍ/ሰላም በወተትና በማር ሀብትም በጣም የታውቀች ከተማ ናት። በከተማዋ አንድ ሁለተኛ ደረጃና አንድ መሰናዶ ትመሀርት በቶች አንዲሁም አንድ መምህራን ማሰልጠኛ ኮለጅ ይግኛሉ።
|
ጋምቤላ (ከተማ) <Gambela>
ጋምቤላ በምዕራብ ኢትዮጵያ የምትገኝ ከተማ ስተሆን ጋምቤላ ሕዝቦች ክልል ዋና ከተማ ናት። በላቲቱድና በሎንጂቱድ 8°15′ ሰሜን ኬክሮስ እና 34°35′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ትገኛለች።
በ1998 የማዕከላዊ የስታትስቲክ ትመና መሰረት የ31,282 ሰዎች መኖሪያ ስትሆን ከነሱም መሃከል 16,163 ወንዶችና 15,119 ሴቶች ይገኙባታል። ጋምቤላ የአኑአክና የኑር ጎሳዎች መኖሪያ ስትሆን የየራሰችው ገበያ በጋምቤላ አላችው። ከተማዋ የአንድ ኤርፖርት ባለቤትና የጋምበላ ብሄራዊ ፓርክ ተጓዳኝ ናት።
ታሪክ
ጋምቤላ የተመሰረተችብት ምክኒያት በባሮ ወንዝ ላይ ባላት አቀማመጥ ነው። ይህ ወንዝ በግዜ ኢትዮጵያና እንግሊዝ ቡና ወዘተ. ወደ ሱዳንና ወደ ግብጽ ለመላክ ምቹ መንገድ መሆኑን ሁለቱም በማመናችው ነው። በ1902 እ.ኤ.አ. አጼ ምኒልክ ለእንግሊዝ ባሮ ወንዝ ላው አንድ ወደብ እንዲጠቀም ይፈቅዱና በ1907 እ.ኤ.አ. በስራ ላይ ከቀረጥ ቢሮ ጭምር ይውላል። በሱዳን የምድር ባቡር ኩባንያ የሚተዳደር የመርክብ አገልግሎት 1,366 ኪሎ ሜትር በመጓዝ ጋምቤላን ከካርቱም ጋር ያገናኛታል።
በሪቻርድ ፓንክርስት ዝገባ መሰረት በክረምት በወር ሁለት ግዜ መርከቦች ሲመላለሱ ወንዙን ሲወርዱ 7 ቀናት፣ ሲወጡ ደግሞ 11 ቀናት ይፈጅባቸው ነበር።
ጋምቤላ በጣሊያን የምሰራቅ አፍሪካ ግዛት በ1936 እ.ኤ.አ. ተጠቃላ፥ በ1941 እ.ኤ.አ. በአንድ ከባድ ውጊያ በኋላ ወደ እንግሊዝ አስተዳደርነት ትዘዋውራ ነበር። ሱዳን ነጻ በወጣችበት በ1948 ዓ.ም. ለኢትዮጵያ ተመለሰች። በባሮ ላይ ያለው ወደብ በደርግ ግዜ እንደተዘጋ ሆኖ፥ ይከፈት ይሆናል የሚል ተስፋ አለ።
|
ጎርጎራ <Gorgora>
ጎርጎራ ወይም ጐርጎራ (የድሮው ጎርጎራ) በጣና ሐይቅ ሰሜን የሚገኝ ልሳነ ምድርና ከተማ ነው። ጎርጎራ ከማሪያም ግምብ (አዲሱ ጎርጎራ) 5ኪሎ ሜትር በስተ ሰሜን ምስራቅ ሲገኝ፣ ከደብረሲና ደግሞ 5ኪሎሜትር በስተ ምዕራብ ይገኛል።
ታሪክ
እድሜያቸው ከ140፣000 እስከ 230፣000 የሚገመቱ የድንጋይ መሳሪያወች በጎርጎርጎራ እንደተገኙ ይጠቀሳል። ከክርስቶስ ልደት በፊት 7000 ዓ.ዓ. ጀምሮ የሸክላ ስራ ውጤቶች በአካባቢው ይመረቱ እንደነበር ከአካባቢው በተገኙ ናሙናወች ተነስቶ የኖርዲክ አፍሪካ ኢንስቲቱት ይዘግባል
ወደ ቅርቡ ዘመን ስንመጣ፣ ጎርጎራ በዐፄ በእደ ማርያም ዜና መዋዕል ላይ ተጥቅሶ የሚገኝ ሲሆን፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ ለጥንቶቹ የኢትዮጵያ መሪዎች ማረፊያ እየሆነ መጥቶ በመጨረሻ በአጼ ሱሰንዮስ የአገሪቱ ዋና ከተማ ለመሆን የበቃ ክፍል ነው። የመንዳባ ገዳም በዚሁ ልሳነ ምድር ሲገኝ፣ በ1924 አካባቢውን ጎብኝቶ የነበረው የእንግሊዙ ቺዝማን የገዳሙ አለቃ ፍጹም ስልጣን የነበራቸውና ህግን አምልጦ ገዳሙ ውስጥ የተጠለለ ሰው ማንም እንደማይነካው እንደነበር ይዘግባል[3]። አጼ ሱሰንዮስዋና ከተማቸውን በ1604 ከጉዛራ ወደ ጎርጎራ እንዳዛወሩ በታሪክ ይጠቀሳል። በኋላም በልጃቸው በፋሲልደስ ዘመን መጀመሪያ በዋና ከተማነት የቀጠለ ቢሆንም ቅሉ አጼ ፋሲል ጎንደር ከተማን በዋና ከተማነት በመቆርቆራቸው ዋና ከተማነቱ አቆመ። ለከተማው መዛወር የወባ በሽታ በአካባቢው መኖር እንደምክንያትነት ይገመታል።
|
ሐረር <Harar>
ሐረር ከአዲስ አበባ ደቡብ ምስራቅ በአምስት መቶ ኪሎሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ የምስራቅ ኢትዮጵያ ከተማ ናት። በዘመኑ የአስተዳደር መዋቅር የሃረሪ ክልል ዋና ከተማ ናት። በ1,885 ሜትር ከፍታ ላይ፣ የወይና ደጋ የአይር ጠባይ በተላበሰ ቦታ ላይ አርፋለች። በምድር መጋጠሚያ ውቅር 9°19′ ሰሜን ኬክሮስ እና 42°07′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ናት። በ1987 ዓመተ ምህረቱ የህዝብ ቆጠራ መሰረት ሐረር 76,378 ሕዝብ ይኖርባታል።
ሐረር ለዘመናት ከፍተኛ የንግድ ማዕከል ሆና ስትኖር ከመሃል አገር፣ ከአፍሪካ ቀንድ እና ከአረብ አገራት ጋር በንግድ መንገዶች ስትገናኝ ከቀሪው አለም ጋር ደግሞ በቀይ ባህር ወደቦች አማካኝነት ትገናኝ ነበር።
የሐረር ጀጎል ግንብ ከ1998 ጀምሮ በዩኔስኮ የዓለም ቅርስ ዝርዝር ውስጥ ይገኛል። በእስልምና ሃይማኖት "4ኛዋ የተቀደሰች ቦታ" ተብላም ስትታወቅ 82 መስጊዶች፤ አንዳንዶቹ ከ10ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ የነበሩ፤ እንዲሁም 102 የቀብር ቦታዎች አሉዋት።
|
ሆሣዕና <Hosaena>
ሆሳዕና በኢትዮጵያ የደቡብ ብሄር ብሄረስቦችና ሕዝቦች ክልል በሀዲያ ዞን የሚገኝ ከተማ ነው። በ1998 ማዕከላዊ የስታትስቲክስ ባለስልጣን እንደተመነው የ57,439 ሰው መኖሪያ ሲሆን ከነሱም 28,163 ወንዶችና 29,276 ሴቶች ይገኙበታል።
በሌላ ገለልተኛ ትምና ደግሞ የ65,317 ሰው መኖሪያ ተደርጎ ተገምቷል። የከተማው አቀማመጥ በ7°34′ ሰሜን ኬክሮስ እና 37°52′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ነው።
|
ጅጅጋ <Jijiga>
ጅጅጋ በምስራቅ ኢትዮጵያ የሚገኝ ከተማ ነው። ከተማው ከሐረር 80 ኪ.ሜ. ይርቃል። በቀድሞው ሐረርጌ ክፍለ-ሀገር የሚገኝ ከተማ ሲሆን አሁን የሶማሌ ክልል ዋና ከተማ ነው። በ1994 እ.ኤ.አ. ከተማው 56,821 ሰዎች ነበሩት። በ1998 ማዕከላዊ የስታትስቲችስ ባለስልጣን እንደተመነው ጅጅጋ የ98,076 ሰው መኖሪያ ስትሆን ከነሱም 50,355 ወንዶችና 47,721 ሴቶች ይገኙበታል። ከተማው በ9°10' ሰሜን ኬክሮስ እና 42°48' ምስራቅ ኬክሮስ ይገኛል።
|
ጅማ <Jimma>
ጅማ (ኦሮምኛ፦ Jimma) በምዕራብ ኢትዮጵያ ካሉት ከተሞች በስፋት ያላቀች ከተማ ናት። በኦሮሚያ ክልል በጅማ ዞነ ስተገኝ በላቲቱድና ሎንጂቱደ 7°40′N 36°50′E ላይ ናት። የቀድሞው ከፋ ክፍለ ሃገር ዋና ከተማ ሆና አገልግላለች።
የብሔራዊ የስታትስቲክ ባለስልጣን በ1998፥ የ159,009 ሕዝብ መኖሪያ ከነሱም መካከል 80,897 ውንዶችና 78,112 ሴቶች መሆናቸውን ተምኗል። ሄርበርት ሉዊስ በ1950ዎቹ የምእራብና ደቡብ ኢትዮጵያ አንጋፋ ገበያ ሲላት በአንድ የበጋ ቀን እስክ ሰላሳ ሺህ ሰው ትስብ እንደነበር ይናገራል። በጅማ የቀድሞ የጅማ ንግስታ የገነቧችው አንዳንድ ቅሪቶች እንደ የአባ ጅፋር ቤተ መንግስት ዛሬ ይታያሉ። ከተማዋ የአንድ ሙሲየም የጅማ ዩኒቨርስቲ የተለያዩ ገበያዎችና የአንድ ኤርፖርት መቀመጫ ናት።
|
ኮምቦልቻ <Kombolcha>
ኮምቦልቻ በኢትዮጵያ የአማራ ክልል ከተማና ወረዳ ሲሆን በደቡብ ውሎ ይገኛል። በ1998 ማዕከላዊ የስታትስቲክስ ባለስልጣን እንደተመነው የ68,766 ሰው መኖሪያ ሲሆን ከነሱም 36,102 ወንዶችና 32,664 ሴቶች ይገኙበታል።
በሌላ ገለልተኛ ትምና ደግሞ የ97,038 ሰው መኖሪያ ተደርጎ ተገምቷል። የከተማው አቀማመጥ በ9°27′ ሰሜን ኬክሮስ እና 35°12′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ነው።
|
መተማ <Matemma>
መተማ (ወይም መተማ ዮሐንስ) በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ በሱዳን ጠረፍ ላይ ያለች መንደር ናት። በአማራ ክልል ስሜን ጎንደር ዞን በ12°58′ ሰሜን ኬክሮስ እና 36°12′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ትቀመጣለች። በ1997 የሕዝብ ቁጥር 5581 ነበረ። ከጠረፉ ፊት ለፊት በሱዳን ውስጥ ጋላባት የተባለች ሱዳናዊ ከተማ አለች።
|
ሞጆ <Mojo>
ሞጆ በኢትዮጵያ የኦሮሚያ ክልል ከተማ ሲሆን በምስራቅ ሸዋ ዞንና በሉሜ ወረዳ ይገኛል። በ1998 ማዕከላዊ የስታትስቲክስ ባለስልጣን እንደተመነው የ39,316 ሰው መኖሪያ ሲሆን ከነሱም 19,278 ወንዶችና 20,038 ሴቶች ይገኙበታል።
በሌላ ገለልተኛ ትምና ደግሞ የ34,411 ሰው መኖሪያ ተደርጎ ተገምቷል። የከተማው አቀማመጥ በ8°36′ ሰሜን ኬክሮስ እና 39°07′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ነው።
|
ሞጣ ከተማ የምትገኘው በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምስራቅ ጎጃም ዞን፣ ሞጣ ወረዳ ከአዲስ አበባ በ371 ኪሜ ከክልሉ መንግስት መቀመጫ ከሆነችው ባህርዳር ከተማ ደግሞ 120 ኪሜ ርቀት ላይ ነው። አስትሮኖሚያዊ መገኛ ቦታዋ ደግሞ 11º 04’ ምስራቅ ላቲቲዩድ እና በ37º 52’ ሰሜን ሎንጊትዩድ ነው።
ሞጣ ከተማ የተቆረቆረችው በ 1747 ዓም ነው።
በ2005 ዓ.ም በማዕከላዊ የስታቲስቲክስ ባለስልጣን በተካሄደው የህዝብ ትንበያ መሰረት የከተማዋ ነዋሪ ህዝብ ብዛት 33,500 ነበር። ከዚህም ውስጥ 17060 (51%) ወንዶችና 16440 (49%) ሴቶች ናቸው፡፡
|
ነቀምት በኢትዮጵያ የኦሮሚያ ክልል ከተማ ሲሆን በምሥራቅ ወለጋ ዞንና በጉቶ ዋዦ ወረዳ ይገኛል። በ1998 ማዕከላዊ የስታትስቲክስ ባለስልጣን እንደተመነው የ84,506 ሰው መኖሪያ ሲሆን ከነሱም 42121 ወንዶችና 42,385 ሴቶች ይገኙበታል።
በሌላ ገለልተኛ ትምና ደግሞ የ76,727 ሰው መኖሪያ ተደርጎ ተገምቷል። የከተማው አቀማመጥ በ9°05′ ሰሜን ኬክሮስ እና 36°32′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ነው። ነቀምት እያድጉ ክክካልልሉ
|
ሻሸመኔ <Shashamane>
ሻሸመኔ በኢትዮጵያ የኦሮሚያ ክልል ከተማ ሲሆን በምስራቅ ሸዋ ዞንና በሻሸመኔ ወረዳ ይገኛል። በ1998 ማዕከላዊ የስታትስቲክስ ባለስልጣን እንደተመነው የ93,156 ሰው መኖሪያ ሲሆን ከነሱም 46,882 ወንዶችና 46,274 ሴቶች ይገኙበታል።
በሌላ ገለልተኛ ትምና ደግሞ የ85,219 ሰው መኖሪያ ተደርጎ ተገምቷል። የከተማው አቀማመጥ በ7°11′ ሰሜን ኬክሮስ እና 38°35′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ነው።
|
እንዳስላሴ በኢትዮጵያ የትግራይ ክልል ከተማ ሲሆን በምዕራባዊ ዞንና በታህታይ ቆራሮ ወረዳ ይገኛል። በ1998 ማዕከላዊ የስታትስቲክስ ባለስልጣን እንደተመነው የ43,967 ሰው መኖሪያ ሲሆን ከነሱም 21,333 ወንዶችና 22,634 ሴቶች ይገኙበታል።. የከተማው አቀማመጥ በ13°52′ ሰሜን ኬክሮስ እና 39°44′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ነው።
|
ሶዶ በኢትዮጵያ የደቡብ ብሄር ብሄረስቦችና ሕዝቦች ክልል ከተማ ሲሆን በሰሜን ኦሞ ዞንና በሶዶ ዙሪያ ወረዳ ይገኛል። በ1998 ማዕከላዊ የስታትስቲክስ ባለስልጣን እንደተመነው የ65,737 ሰዎች መኖሪያ ሲሆን ከነሱም 34,069 ወንዶችና 31,668 ሴቶች ይገኙበታል።
በሌላ ገለልተኛ ትምና ደግሞ የ53,149 ሰው መኖሪያ ተደርጎ ተገምቷል። የከተማው አቀማመጥ በ8°35′ ሰሜን ኬክሮስ እና 35°49′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ነው።
በሌላ በኩል ሶዶ ማለት የጉራጌ ብሄረሰብ የጎሳ ስም ነው።
|
ጢያ በደቡብ ኢትዮጵያ የሚገኝ ከተማ ነው። በጉራጌ ዞን ስር ሲመደብ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ውስጥ ይገኛል።
ጢያ የሚታወቀው ከአጠቅገቡ በሚገኘው ታሪካዊ ቅርስ ነው። በዚህ ቦታ 36 እራሳቸውን ችለው የቆሙ የደንጊያ ሃውልቶች ሲገኙ፣ 32ቱ ትርጉማቸው በውል የማይታውቅ ቅርጻ ቅርጾች፣ እንደ ጎራዴ ምስል ያሉ በላያቸው ላይ ሰፍረውባቸው ይገኛሉ። እንዳንድ ተማሪዎች አገላለጽ እኒህ ቦታወች የመቃብር ቦታ ነበሩ [1] ። የጀርመን ብሔር አጥኝዎች እኒህን ሃውልቶች በ1927 እንዳጠኑ ይዘገባል። ከ1972ዓ.ም. ጀምሮ አካባቢው በዩኔስኮ የአለም ቅርስ ተደርጎ ተመድቧል።
ሌሎች ከጢያ አጠገብ የሚገኙ መስህቦች መልካ አዋሽና ሔራ ሸጣን እና አገሶቄ ይጠቀሳሉ።
እንደ 1997 የህዝብ ቆጠራ፣ ጢያ ውስጥ 3፣363 ሰዎች ይኖሩ ነበር።
|
ወልወል በምሥራቅ ኢትዮጵያ ፥ በሶማሌ ክልልውስጥ የምትገኝ ከተማ ነች ። ከተማዋ ከባህር ወለል በአምስት መቶ ሰባ ሜትር ከፍታ ላይ የምትገኝ ስትሆን 7°03′ ሰሜን ኬክሮስ እና 45°24′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ትገኛለች።
ኅዳር ፲፬ ቀን ፲፱፻፳፯ ዓ/ም በኦጋዴን ክልል በኢትዮጵያ እና በኢጣሊያዊ ሶማልያ ያለውን ድንበር እንዲያሠምሩ የተላኩት የብሪታንያ እና የኢትዮጵያ ልዑካን በዚሁ ክልል ውስጥ ለሥራ ይዘጋጁ ነበር። በዚህ ጊዜ ‘ሙስቲ’ በሚባል የኢጣሊያ መቶ ዓለቃ የሚታዘዙ ሁለት መቶ ሶማሌያዊ ወታደሮች የኢትዮጵያን ድንበር ጥሰው፤ ከሺህ በላይ የውሐ ጉድጓዶች የነበሯትን፤ በኢትዮጵያ ክልል ውስጥ ያለችውን ወልወልን ከበዋት ተገኙ። በወቅቱ የኦጋዴን ገዥ የነበሩት የፊታውራሪ ሺፈራው ወታደሮችና የኢጣልያን ወገን በሚመራው በሻለቃ ቺማሩታ ወታደሮች ለሁለት ሣምንታት ከተፋጠጡ በኋላ በኢትዮጵያና በፋሽስታዊ ኢጣልያ መካከል ለአምሥት ዓመታት የተከተለው ጦርነት ክብሪት ተጫረ።
የፋሺስት ኢጣሊያ መሪ ቤኒቶ ሙሶሊኒ ለብዙ ዓመታት አገራችንን በኃይል ወርሮ ቅኝ ግዛት ለማድረግ ሲያቅድ የነበረውን ዓላማ በዚህ ግፍ ካካሄደ በኋላ በዓመቱ በጥቅምት ፲፱፻፳፰ ዓ.ም. በዚያው በኦጋዴን መሥመር ወረረ።
|
ይርጋለም <Yirga Alem>
ይርጋ አለም በኢትዮጵያ የደቡብ ብሄር ብሄረስቦችና ሕዝቦች ክልል ከተማ ሲሆን በሲዳማ ዞንና በዳሌ ወረዳ ይገኛል። በ1998 ማዕከላዊ የስታትስቲክስ ባለስልጣን እንደተመነው የ43,815 ሰው መኖሪያ ሲሆን ከነሱም 21,840 ወንዶችና 21,975 ሴቶች ይገኙበታል።
በሌላ ገለልተኛ ትምና ደግሞ የ36,268 ሰው መኖሪያ ተደርጎ ተገምቷል። የከተማው አቀማመጥ በ6°45′ ሰሜን ኬክሮስ እና 38°25′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ነው።
|
ይርጋለም |
|
|
|
0 comentários:
አስተያየት ይለጥፉ