ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ ወይም በይፋ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ (ኢ.ፌ.ዲ.ሪ.) በአፍሪካ ቀንድ የምትገኝ የረጅም ዘመን ታሪክ ያላት ሀገር ናት። በአፍሪካ ነፃነታቸውን ጠብቀው ለመኖር ከቻሉ ሁለት አገሮች አንዷ ነች። በህዝብ ብዛት ከአፍሪካ ኢትዮጵያ ሁለተኛ ስትሆን ፣ በቆዳ ስፋት ደግሞ አስረኛ ናት። ዋና ከተማዋ አዲስ አበባ ናት።
አብዛኛዎቹ የአፍሪካ ሀገሮች ዕድሜያቸው ከአንድ ምዕተ-ዓመት የሚያንስ ሲሆን ፣ ኢትዮጵያ ግን ከጥንት ጊዜ ጀምሮ በንጉሠ-ነገሥታት እና ንግሥተ-ነግሥታት የተመራች ሀገር ናት። የሰለሞናዊው ሥርወ-መንግሥት የአመጣጡን ዘር እስከ አስረኛው ዓመተ-ዓለም ድረስ ይቆጥራል። ኢትዮጵያ የሰው ልጅ ከጥንት ጊዜ ጀምሮ የኖረባት ቦታ እንደሆነች ብዙ የሳይንሳዊ መረጃ ተግኝቷል። በበርሊን ጉባኤ በኩል የአውሮፓ ሀያላት ሀገሮች አፍሪካን ሲከፋፍሏት፣ ኢትዮጵያ ነፃነቷን ጠብቃለች። የሊግ ኦፍ ኔሽንስ (League of Nations) አባል ከነበሩት ሶስት የአፍሪካ ሀገሮች አንዷ ነበረች። ከአጭር የኢጣልያ ወረራ ጊዜ በኋላም ከየተባበሩት መንግሥታት መሥራቾች አንዷ ናት። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ብዙ የአፍሪካ ሀገራት ነፃነታቸውን ሲያገኙ ፣ ሰንደቅ-አላማቸውን በኢትዮጵያ ቀለሞች ማለትም በአረንጓዴ ፣ ቢጫ እና ቀይ ላይ ነው የመሠረቱት። አዲስ አበባ ደግሞ ለየተለያዩ በአፍሪካ ላይ ላተኮሩ አለም አቀፍ ድርጅቶች መቀመጫ ሆነች።
የዛሬዋ ኢትዮጵያ የትልቅ የግዛት ለውጥ ውጤት ናት። ከሰሜን ግዛቱዋ በጣም የተቀነሰ ሲሆን በደቡብ በኩል ደግሞ ተስፋፍቷል። በ ፲፱፻፷፯ (1967) ዓ.ም.፣ ግርማዊ ቀዳማዊ ዓፄ ኃይለ ሥላሴ ከሥልጣን ሲወርዱ ፣ የእርስ በርስ ጦርነት በሀገሩ ተባባሰ። ከዚህ ጊዜ በኋላ ኢትዮጵያ በተለያዩ የመንግሥት አይነቶች ተዳድራለች። ዛሬ አዲስ አበባ የአፍሪካ ሕብረት (African Union) እና የተባበሩት መንግሥታት የኢኮኖሚክ ኮሚሽን ለአፍሪካ መቀመጫ ናት። የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት ከአፍሪካ ኃያል ሠራዊቶች አንዱ ነው። ኢትዮጵያ በአፍሪካ የራሷ ፊደል ያላት ብቸኛ ሀገርም ናት።
ኢትዮጵያ ተፈጥሮ ያደላት ሀገር ናት። ከአፍሪካ ትልልቅ ተራራዎች እንዲሁም ከዓለም ከባህር ጠለል በታች በጣም ጥልቅ ከሆኑ ቦታዎች አንዳንዶቹ ይገኙባታል። ሶፍ ዑመር ከአፍሪካ ዋሻዎች ትልቁ ሲሆን ፣ ዳሎል ከዓለም በጣም ሙቅ ቦታዎች አንዱ ነው። ወደ ሰማንኒያ የሚቆጠሩ ብሔሮችና ብሔረሰቦች ዛሬ በኢትዮጵያ ይገኛሉ። ከነዚህም አማራና ኦሮሞ በብዛት ትልቆቹ ናቸው። ኢትዮጵያ ከአንድ ድንጋይ ተፈልፍለው በተሰሩ ቤተ-ክርስትያኖቹዋ እና በኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳልያ አሸናፊ አትሌቶቹዋ ትታወቃለች። የቡና ፍሬ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘው በኢትዮጵያ ሲሆን ሀገሪቱዋ በቡናና ማር አምራችነት በአፍሪካ ቅድሚያ ትይዛለች።
ኢትዮጵያ ከዓለም ሶስቱ ትልቅ የአብርሃም ሀይማኖቶች ጋር ታሪካዊ ግንኙነት አላት። ክርስትናን በአራተኛው ምዕተ-ዓመት ተቀብላለች። ከሕዝቡ አንድ ሶስተኛው እስላም ነው። የመጀመሪያው የእስላም ሂጅራ ወደ ኢትዮጵያ ነው የተከናወነው። ነጋሽ በአፍሪካ የመጀመሪያው የእስላም መቀመጫ ናት። እስከ ፲፱፻፸ ዎቹ ድረስ ብዙ ቤተ-እስራኤሎች በኢትዮጵያ ይኖሩ ነበር። የራስ ተፈሪ እንቅስቃሴ ኢትዮጵያን በትልቅ ክብር ነው የሚያያት።
ግርማዊ ቀዳማዊ ዓፄ ኃይለ ሥላሴ ከስልጣን ከወረዱ በኋላ ድህነት በኢትዮጵያ በጣም ተስፋፍቶ ነበር። ሰማኒያ አምስት ከመቶ በላይ የሚሆነው የናይል ወንዝ ውሀ ከሀገሩ የሚመጣ ቢሆንም በ ፲፱፻፸ ዎቹ በተከሰቱ ድርቆች በብዙ የሚቆጠሩ ሰዎች ሞተዋል። ነገር ግን ቀስ በቀስ ሀገሩዋ እያገገመች ነው። ዛሬ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በአፍሪካ ውስጥ በፍጥነት ከሚያድጉት አንዱ ነው።
|
ስያሜ
ኢትዮጵያ የሚለው ቃል አመጣጥ በተለያዩ የታሪክ ምሁራን የተለያየ ገለፃ ሲኖረው በጣም ተአማኒነት ካገኙት አንዱ አይቲዮፒያ (የግሪክ ቃል) የሚለው ቃል ነው።
ኢትዮጵያ ድሮ ለውጭ አገራት አቢሲኒያ በሚል መጠሪያ ትታወቅ ነበር ፤ ይህም ስያሜ የመጣ ከሀበሻ ነበር።
ኢትዮጵያ የሚለው ስም ጥንታዊነት የሚታወቅ ከግሪክ ጸሐፍት ነው። ከሁሉ ቀድሞ የሆነው ግሪክ ባለቅኔ ሆሜር (፰፻ ዓክልበ. ያሕል) ይጠቅሰዋል። በግሪክ አጠቃቀም ከሳህራ በረሃ በስተደቡብ ላለው የአፍሪካ አህጉር ክፍል በሙሉ ሲገልጽ ፣ በተለይ ለኩሽ በሚነካ ትርጉሞች ይገኛል። ፕሊኒ እንደሚለው ፣ ቃሉ የመጣ አይቲዮፕስ ከተባለ ግለሠብ ነበር። እንዲሁም በኢትዮጵያ መጽሐፍት ልማድ የሀገሩ ስም የኩሽ ልጅ ኢትዮጲስ ሞክሼ ነው። ሆኖም በአቅራቢያው እንደ መንግሥት ስም መጀመርያ የተመዘገበው ዘመን የአክሱም ንጉሥ ኤዛና ዘመነ-መንግሥት (፬ኛው ክፍለ ዘመን ዓ.ም.) ነበር።
አንዳንድ የኢትዮጵያ ጸሐፊ «ኢቅጢዮፋጊ» («አሣ በሎች») የሚለው ግሪክኛ ስም የ«ኢትዮጵያ» ድጋሜ ሆኖ የስያሜው ጥንታዊነትና ኗሪነት ምስክር ነው የሚል አሣብ አቅርበዋል። በዚህ አሣብ ስሙ በውነት «ዕንቁ» «ቶጳዝዮን» ከሚሉ ቃላት ጋር ዝምድና እንዳለው ባዮች ናቸው። መጽሐፈ ኢዮብ ፳፰፡፲፱ ደግሞ «የኢትዮጵያ (የኩሽ) ቶጳዝዮን» ይጠቅሳል።
በ፱ኛው ክፍለ ዘመን ዓ.ም. የቢዛንታይን ሊቃውንት በጻፉት ሃልዮ ዘንድ ፣ «አይቲዮፒያ» የሚለው ስም የመጣ ከግሪኩ ቃላት «አይቶ» (አቃጥላለሁ) እና «ኦፕስ» (ፊት) ነበር። ይህ አስተሳሰብ እስካሁን ድረስ በምዕራብ ሊቃውንት ተቀባይነት አለው።
ታሪክ ቅድመ ታሪክ
ኢትዮጵያ ከጥንት ጀምሮ የሰው ልጅ ከነበረባችው ቦታዎች አንዷ መሆኗ ትታወቃለች። የሰው ፍልሰት ጥናቶች ፣ የቅሪተ አካል ጥናቶችና ሌሎች የሳይንሳዊ ዘዴዎች ይህን ያረጋግጣሉ። ድንቅነሽ የምትባለው በአፋር ክልል ውስጥ የተገኘችው አጽም በአለም በዕድሜ ሁለተኛ ጥንታዊ ናት። ከ 3.2 ሚሊዮን ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ እንደኖረች ይገመታል። ሌሎችም ታዋቂ አጽሞች በኢትዮጵያ ተገኝተዋል።
የመጀመሪያዎቹ መንግስታት
በ ፰፻ (800) ዓመተ-ዓለም አካባቢ ደአማት የሚባል መንግስት በሰሜን ኢትዮጵያና ኤርትራ ተቋቋመ። በሰሜን ኢትዮጵያ የምትገኘው የሀ የደአማት ዋና ከተማ ነበረች። በየመን የሚኖሩት ሳባውያን በደአማት ላይ ተፅዕኖ እንደነበራቸው የሚታመን ሲሆን ይህ ተፅዕኖ ምን ያህል እንደሆነ ግን በእርግጥ አይታወቅም። ወደ ፬፻ (400) ዓመተ-ዓለም አካባቢ የደአማት መንግስት ከስልጣን ሲወድቅ በትናንሽ መንግስቶች ተተካ። ከነዚህ ትናንሽ መንግስቶች አንዱ አክሱም ሲሆን አካባቢውን እንደገና በአንድነት ለመግዛት ችሎ ነበር።
የአክሱማውያን ስፈን በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ጠንካራ መንግሥታዊ ማኅበረሰብ ነበር። በፋርስ ፣ ሮማ እና ቻይና ይገኙ ከነበሩ ታላላቅ መንግሥታት በወደረኛነት የሚቆጠር ትልቅ ኅይል ነበር። በ4ኛው ምእተ-ዓመት አክሱም ወደ ክርስትና ተለወጠ። በ፮ኛው ምእት ዓመት የአክሱማውያን ግዛታዊ ቁጥጥር የዛሬዋን የመን ግዛት ይጨምር ነበር። ግን በ፮ኛው እና በ ፰ኛው አምኣት የአክሱም ሥልጣኔ በእስልምና መነሣት እና መስፋፋት ተዳክሞ ለውድቀት በቃ ። ተከታዩ የዛጔ ሥርወ-መንግሥት ልክ በድንገት እንደተነሳ በድንገት ሲያበቃ ፣ ይኵኖ አምላክ ሥልጣን በ ፲፪፻፷፪ (1262) ዓ.ም. ጨበጡ ፤ እንዲያም ሲል የሰለሞናዊው ሥርወ-መንግሥትን መለሱ።
|
ከአውሮፓ ጋር የታደሰ ግንኙነት
በ ፲ ፭ኛው ምዕተ-ዓመት መጀመሪያ ኢትዮጵያ ከአክሱም ጊዜ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከአውሮፓ ጋር ግንኙነት ጀመረች። ከእንግሊዝ ንጉሥ ሄነሪ አራተኛ (Henry IV) ወደ የአቢሲኒያ ንጉሠ-ነገሥት የተላከ ደብዳቤ እስከ ዛሬ ድረስ አለ። በ ፲፬፻፳፰ (1428) ዓ.ም. እ.ኤ.አ. አፄ ይስሐቅ ወደ የአራጎን ንጉሥ አልፎንዞ አምስተኛ (Alfonso V) ሁለት መልክተኞች ልከው ነበር። ግን የመጀመራያው ያልተቋረጠ ግንኙነት በአፄ ልብነ ድንግል ስር ከፖርቱጋል ጋር ከ ፲፭፻፰ (1508) ዓ.ም. እ.ኤ.አ. ጀምሮ ነው የተካሄደው።
ኢትዮጵያ በአህመድ ግራኝ ስትጠቃ ፣ ፖርቱጋል አራት መቶ ወታደሮችና የጦር መሳሪያ በመላክ ኢትዮጵያን ረድታለች። አፄ ሱስንዮስ በፖርቱጋልና እስፓንያ ተጽዕኖ እና ተጨማሪ እርዳታ ከመፈለጋቸው የተነሳ ወደ የሮማ ካቶሊክ ክርስትና ተለወጡ ፤ የኢትዮጵያ ይፋ ሀይማኖትንም አደረገቱት። ይህ ውሳኔ ወደ ግዙፍ ተቃውሞና ጦርነት አመራ። በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች ከሞቱ በኋላ ፣ የአፄ ሱስንዮስ ልጅ አፄ ፋሲለደስ በ ፲፮፻፴፪ (1632) ዓ.ም. እ.ኤ.አ. ኢትዮጵያ ወደ አርቶዶክስ ክርስትና መመለሷን አወጁ። አውሮፓውያኖቹንም ከኢትዮጵያ አስወጡ።
|
ዘመነ መሳፍንት
ከ ፲፯፻፶፭ (1755) እስከ ፲፰፻፶፭ (1855) እ.ኤ.አ. ኢትዮጵያ እንደገና ከአለም ጉዳዮች ተገላ ነበር። ይህ ጊዜ «ዘመነ-መሳፍንት» ይባላል ምክኒያቱም የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥቶች በራስ ሚካኬል ስሁል ፣ ራስ ወልደ ሥላሴ ፣ ራስ ጉግሳ እና በመሳሰሉት ቁጥጥር ስር ነበሩ። ራስ ጉግሳ በ፲፯ኛው ክፍለ ዘመን ጎንደርን በመምራታቸው የቤተ-መንግሥቱን ቋንቋ ከአማርኛ ወደ ኦሮምኛ ለውጠው ነበር።
የኢትዮጵያ ግለልኘነት ያበቃው ከእንግሊዝ ጋር ግንኙነት ስትጀምር ነው። ኢትዮጵያ እንደገና የተዋሀደችው እንዲሁም የዘውዱ ስልጣን የተጠናከረው በ ፲፰፻፶፭ (1855) እ.ኤ.አ. በአፄ ቴዎድሮስ ምክኒያት ነው። የሰሜን አሮሞዎችና ትግሬዎች አመፅና የግብፆች ተደጋጋሚ ድንበር መጣስ የአፄ ቴዎድሮስ ስልጣን እንዲዳከም አደረጉት። በመጨረሻም ከእንግሊዝ ጋር በነበረው ጦርነት እስረኛ አልሆንም ብለው አፄ ቴዎድሮስ እራሳቸውን አጠፉ። በ ፲፰፻፷፰ (1868) እ.ኤ.አ. ኢትዮጵያና ግብፅ ጉራ በሚባለው ቦታ ተዋጉ። በአፄ ዮሐንስ አራተኛ የተመሩት የሰሜን ኢትዮጵያ ኃይሎች ድል ተቀናጁ።
በ ፲፰፻፹፱ (1889) እና በ ፲፰፻፺ (1890) ዎቹ እ.ኤ.አ. መጀመሪያ ፣ የሸዋ ንጉሥ ሳህለ ሥላሴ ከዚያም ዳግማዊ አፄምኒልክ በራስ ጎበና እርዳታ አማካኝነት ሀገሯን ወደ ደቡብና ምሥራቅ ማስፋፋት ጀመሩ። ከአህመድ ግራኝ ወረራ በኋላ በኢትዮጵያ ቁጥጥር ስር ያልነበሩ ፣ ሌሎች ደግሞ በማንኛው ጊዜ በኢትዮጵይ ቁጥጥር ስር ያልነበሩ ቦታዎች በዳግማዊ አፄ ምኒልክ አገዛዝ ጊዜ በኢትዮጵያ ስር ሆኑ። ከዚህ ጊዜ በኋላ የኢትዮጵያ ድንበር ብዙ አልተለወጠም። ከ ፲፰፻፹፰ (1888) እስከ ፲፰፻፺፪ (1892) እ.ኤ.አ. ድረስ የነበረው የሰፋ ድርቅ ከኢትዮጵያ ህዝብ በአንድ ሶስተኛ የሚገመተውን ቀጥፎአል።
|
የአውሮፓ ሽሚያ ለአፍሪካ
በ ፲፰፻፹ (1880) ዎቹ እ.ኤ.አ. የአውሮፓ መንግሥቶች በበርሊን ጉባኤ ተስማምተው አፍሪካን በቅኝ ገዢነት መከፋፈል ጀመሩ። በኢትዮጵያ እና ጣልያን መካከል የነበሩ የዚያ ዘመን ውዝግቦች ወደ አድዋ ጦርነት በ ፲፰፻፹፰ (1888) ዓ.ም. አመሩ። በጦርነቱ የጣልያን ትልቅ ዘመናዊ ጦር በኢትዮጵያ ጦር ትልቅ ሽንፈት የደረሰበት መሆኑ ዓለምን አስደነቀ።
|
አዲስ አበባ |
|
የግርማዊ ቀዳማዊ ዓፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመን
በ ፳ኛው ምእት ሁለተኛው ሩብ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ኢትዮጵያን ከልጅ ኢያሱ በኋላ መምራት ጀመሩ። ዓፄ ኃይለ ሥላሴ ለአፍሪካ ሕብረት መቋቋም ትልቅ ሚና ተጫውተዋል።
የኢትዮጵያ ነጻነት በጣልያን ወረራ ከ ፲፱፻፴፮ (1936) እስከ ፲፱፻፵፩ (1941) እ.ኤ.አ. ድረስ ቢጠቃም በጀግኖችዋ መከታ ተጠብቋል። በአዚህ ጥቃት ጊዜ ዓፄ ኃይለሥላሴ በ ፲፱፻፴፭ (1935) እ.ኤ.አ. በሊግ ኦፍ ኔሽንስ (League of Nations) ፊት የሚታወስ ንግግር በአማርኛ አደረጉ። ይህ ንግግር በዓለም ታዋቂ አደረጋቸው። እንዲሁም በ ፲፱፻፴፭ (1935) እ.ኤ.አ. በ ታይም (Time) መጽሄት «የዓመቱ ሰው» አስባላቸው። ጣልያን ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ውስጥ መሳተፍ ስትጀምር ፣ እንግሊዝ ከኢትዮጵያዊ ተዋጊዎች ጋር ኢትዮጵያን ነጻ አወጣች። ግን እስከ ፲፱፻፵፫ (1943) እ.ኤ.አ. ድረስ አንዳንድ ጣልያኖች በደፈጣ ያለ ስኬት ይዋጉ ነበር። በ ፲፱፻፵፪ (1942) እ.ኤ.አ. ዓፄ ኃይለ ሥላሴ ባርነት እንደ ተከለከለ አወጁ።
ዓፄ ኃይለ ሥላሴ ጀግና ሆነው ቢታዩም ፣ የ ፲፱፻፸፫ (1973) እ.ኤ.አ. ዓለም አቀፍ የነዳጅ ቀውስ ፣ የምግብ ዕጥረትና የድንበር ጦርነቶች ተቃውሞ አስነሱ። ከዚያም በ ፲፱፻፸፬ (1974) እ.ኤ.አ. በሶቪየት ሕብረት የተደገፈውና በመንግስቱ ኃይለ ማርያም የተመራው ደርግ (ደርግ ማለት ኮሚቴ ማለት ነው) ዓፄ ኃይለ ሥላሴን ከስልጣን አስወረደ።
|
ኮምዩኒዝም
የተለያዩ መፈንቅለ መንግሥቶች ፣ የሰፋ ድርቀትና ስደተኞች የደርግ ሥርዓት ትልቅ ችግሮች ነበሩ። በ ፲፱፻፸፯ (1977) እ.ኤ.አ. ሶማሊያ ኦጋዴንን በመውረሯ የኦጋዴን ጦርነት ተነሳ። በሶቪየት ሕብረት ፣ ኩባ ፣ ደቡብ የመን ፣ ምስራቅ ጀርመንና ሰሜን ኮሪያ የመሳሪያ እርዳታ እንዲሁም ወደ ፲፭ ሺህ በሚቆጠሩ የኩባ ወታደሮች ድጋፍ አማካኝነት ደርግ ኦጋዴንን እንደገና መቆጣጠር ቻለ።
በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች በቀይ ሽብር ፣ የግዴታ ስደት ፣ ወይም ረሀብ ሞተዋል። መንግስቱ ቀይ ሽብር ያካሄደው በተቀዋሚዎች በተፈጸመው ነጭ ሽብር መልስ እንደሆነ ጠቅሷል። በ ፳፻፮ (2006) እ.ኤ.አ. መንግስቱ ኃይለ ማርያም በሌሉበት የሞት ቅጣት ተፈርዶባቸዋል።
በ ፲፱፻፹ (1980) ዎቹ መጀመሪያ የተከሰቱ ድርቀቶች ምክኒያት ስምንት ሚሊዮን የሚሆን ሕዝብ ሲራብ ፣ አንድ ሚሊዮን ደግሞ ሞተዋል። ተቃውሞ በትግራይና ኤርትራ ክልሎች ተስፋፋ። በ ፲፱፻፹፱ (1989) እ.ኤ.አ. ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ከሌሎች እንቅስቃሴዎች ጋር በመቀናጀት የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባርን መሠረተ። የሶቪየት ሕብረትም ለኢትዮጵያ የምታደርገውን ድጋፍ መቀነስ ጀመረች። የኢኮኖሚ ችግሮች ተከሰቱ ፣ እንዲሁም የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት ተዳከመ።
በሜይ ፲፱፻፺፩ (1991) እ.ኤ.አ. የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ. ጦር ወደ አዲስ አበባ አመራ። የመንግስት ኃይሎች ምንም አይነት የውጭ እርዳታ ስላላገኙ ፣ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ.ን ጥቃቶች መቋቋም አልቻሉም። መንግስቱ ኃይለ ማርያም ወደ ዚምባብዌ ሄደው እስከ ዛሬ ድረስ በዛችው ሀገር ይኖራሉ። ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ. ፹ ፯ አባላት ያሉት የሽግግር መንግሥት መሠረተ። በጁን ፲፱፻፺፪ (1992) እ.ኤ.አ. የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ፣ እንዲሁም በማርች ፲፱፻፺፫ (1993) እ.ኤ.አ. የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ኅብረት የሽግግር መንግሥቱን ለቀው ወጡ። በ ፲፱፻፺፬ (1994) እ.ኤ.አ. ሁለት የሕግ አውጪ ምክር ቤቶችንና የፍትሕ ስርዓትን የሚደነግግ አዲስ ሕገ መንግሥት ተፃፈ። የመጀመሪያው ምርጫ በሜይ ፲፱፻፺፭ (1995) እ.ኤ.አ. ተካሄደ። አቶ መለስ ዜናዊ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሁም ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ።
|
በቅርብ ጊዜ
በየተባበሩት መንግሥታት ውሳኔ ኢትዮጵያና ኤርትራ በፌደሬሽን ተዋህደው ነበር። በ ፲፱፻፺፫ (1993) እ.ኤ.አ. በተካሄደውና የተባበሩት መንግሥታት በታዘበው ሕዝበ ድምፅ ፣ ከ ፺፱ ከመቶ በላይ የሚሆነው የኤርትራ ሕዝብና በውጭ ሀገር የነበሩ ኤርትራውያን ከኢትዮጵያ መገንጠልን መርጠዋል። በሜይ ፳፬ ፣ ፲፱፻፺፫ (1993) እ.ኤ.አ. ኤርትራ ከኢትዮጵያ ነፃነቷን አወጀች።
በሜይ ፲፱፻፺፰ (1998) እ.ኤ.አ. የድንበር ውዝግብ እስከ ጁን ፳፻ (2000) እ.ኤ.አ. ወደ ቀጠለው የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት አምርቶአል። ይህ ጦርነት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚን ጎድቶአል። በሜይ ፲፭ ፣ ፳፻፭ (2005) እ.ኤ.አ. አጠቃላይ ምርጫ ቢካሄድም ተቃዋሚዎች ማጭበርበር እንደነበረ ወንጅለዋል። በአጠቃላይ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ከ ፪፻ (200) በላይ የፓርላማ መቀመጫዎችን አሸንፈዋል። ግን አንዳንድ የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ አባሎች ከምርጫው በኋላ ከነበረው ረብሻ ጋር በተያያዘ ታስረው ነበር። በአሁኑ ጊዜ ያለው የፖለቲካ ስርአት በብሄር ላይ የተመሰረተ ፌደራላዊ ስርአት ነው፡፡
|
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ |
|
መልክዓ-ምድር
ኢትዮጵያ በሰሜን ምስራቅ አፍሪካ ከ 3-14 ዲግሪ ሰሜን እና ከ 33-48 ዲግሪ ምሥራቅ የምትገኝ አገር ስትሆን የቆዳ ስፋቱዋም 1,127,127 ካሬ ኪ.ሜ. ነው። በሰሜን ከኤርትራ ፣ በምዕራብ ከሱዳንና ደቡብ ሱዳን ፣ በደቡብ ከኬኒያ ፣ እንዲሁም በምሥራቅ ከጅቡቲ እና ከሶማሊያ ጋር ትዋሰናለች። የኢትዮጵያ አብዛኛው ግዛት በተራሮች እና አንባዎች የተሞላ ሲሆን ፣ ታላቁ የምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ እነዚህኑ ከፍተኛ ቦታዎች ከሰሜን ምሥራቅ ወደ ደቡብ ምዕራብ በመጋደም ለሁለት ይከፍላቸዋል። በስምጥ ሸለቆው ዙሪያም በረሃማ የሆኑ ዝቅተኛ ቦታዎች ይገኛሉ። ይሄን መሰሉ የመልክዓ-ምድር ልዩነት አገሪቷ የተለያዩ የአየር ንብረት ፣ የአፈር ፣ የዕፅዋት እና የሕዝብ አሰፋፈር ገጽታዎች እንዲኖሯት አስችሏታል። በከፍታና በመልክዓ-ምድራዊ አቀማመጥ የተነሣ በኢትዮጵያ ውስጥ ሦስት ዓይነት የአየር-፡ ንብረት ክልሎች ይገኛሉ። እነሱም፦
ደጋ - ከፍታቸው ከባሕር ጠለል 2400 ሜትር የሚጀምር እና የሙቀት መጠናቸው ከ 16 ዲግሪ ሴ.ግ. የማይበልጥ
ወይናደጋ - ከፍታቸው ከባሐር ጠለል ከ 1500 እስከ 2400 ሜትር ፣ ሙቀታቸውም ከ 16 ዲግሪ ሴ.ግ. እስከ 30 ዲግሪ ሴ.ግ. የሚደርስ ፣ እና
ቆላ - ከባህር ጠለል በታች ጀምሮ እስከ 1500 ሜትር ከፍታ ያላቸው ፣ የሙቀት መጠናቸውም ከ 30 ዲግሪ ሴ.ግ. እስከ 50 ዲግሪ ሴ.ግ. የሚደርስ አካባቢዎች ናቸው።
ዋናው የዝናብ ወቅት ከሰኔ አጋማሽ እስከ መስከረም አጋማሽ ሲሆን ፣ ከሱ ቀደም ብሎ አልፎ አልፎ የሚጥል የበልግ ዝናብ በየካቲት እና በመጋቢት ይከሰታል። የተቀሩት ወራት በአብዛኛው ደረቅ ናቸው።
|
ሕዝብ
ኢትዮጵያ ከ ፹ (80) በላይ የሚሆኑ ብሔረሰቦች የሚገኙባት «የብሄረሰቦች ሙዚየም» ልትሰኝ የቻለች ሀገር ነች። ትልልቆቹ ብሄረሰቦች ፣ የአማራ ፣ እና የኦሮሞ የትግራይ እንደሁም የሶማሌ ሲሆኑ እነዚሁ ብሄረሰቦች ከጠቅላላው የአገሪቱዋ ሕዝብ ቁጥር ክ 3/4ኛ በላይ የሚሆነውን ይይዛሉ። በሃይማኖት በኩልም ሁለቱ ትልልቅ ሃይማኖቶች ክርስትና እና እስልምና በስፋት የሚተዋልባት አገር ናት። የእስልምና እምነት ተከታዮች ከ 9%-12.4 % ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ከ 85%-89.5% እንዲሁም የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ወደ 5%-8% የሚሆነውን ይይዛሉ።
ቋንቋዎች
|
ዋና መጣጥፍ፦ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች
በኢትዮጵያ ውስጥ ከ ፹ በላይ ብሔር ብሔረሰቦች የሚኖሩ ሲሆን በቋንቋም በኩል ከ ፹ በላይ የሚሆኑ ቋንቋዎች የሚነገሩባት ሀገር ናት። በአሁኑ ወቅት በአብዛኛው ኢትዮጵያውያን የሚነገሩት ቋንቋዎች አማርኛ እና ኦሮምኛ ሲሆኑ ፤ አማርኛ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል ያሉ ነዋሪዎች የመማሪያ ፤ የመገበያያ እንዲሁም የስራ ቋንቋ ሆኖ የቆየ በመሆኑ በአሁኑ ወቅት የስራ ቋንቋ ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ የሚነገሩት ቋንቋዎች አፍሮ-ኤስያዊ እና ናይሎ ሳህራዊ በሚባሉ ሁለት ዋና የቋንቋ ክፍሎች ሊካተቱ ይችላሉ። በአፍሮ-ኤስያዊ የቋንቋ ቤተሰብ ውስጥም ኩሻዊ፣ ኦሞአዊ እና ሴማዊ የሚባሉ ንዑስ ክፍሎች አሉ።
ኩሻዊ ከሚባሉት ቋንቋዎች ዋና ዋናዎቹ አፋን ኦሮሞ ፣ ሶማልኛ ፣ አፋርኛ ፣ ሲዳምኛ ፣ ሃዲያኛ እና ከምባትኛ ሲሆኑ ከአባይ-ሰሃራዊ የቋንቋ ምድብ የሚካተቱት በርታኛ ፣ ኩናማኛ ፣ ጉሙዝኛ ፣ ሙርሲኛ እና የመሳሰሉት ናቸው። እንደ ወላይትኛ ፣ ጋሞኛ ፣ ከፋኛ ፣ ሃመርኛ የመሳሰሉት የኦሞአዊ ቋንቋ ዘሮች ሲሆኑ አማርኛ ፣ ትግርኛ ፣ ጉራጊኛ ፣ ስልጢኛ ፣ ሀደሪኛ እና መሰል ቋንቋዎች ከሴማዊ ቋንቋዎች ይመደባሉ።
|
ሰንደቅ ዓላማ |
|
ፊደል
የሴሚቲክ ምንጭ ያላቸው እንደ ትግርኛና አማርኛ ያሉት ቋንቋዎች የራሱ የሆነ የተለየ የፊደል ስርአት ያላቸው ሲሆን ይህም ኢትዮጵያን ከአፍሪቃ ብቸኛዋ ባለ ጥንት ፊደል ሀገር ያደርጋታል። እነኚህ የሴሚቲክ ምንጭ ያላችው ቋንቋዎች ግዕዝ የተባለ በአሁኑ ወቅት ከቤተክርስትያን ውጭ ለዕለት ተዕለት ግልጋሎት ላይ የማይውል ግንድ ዘር አላቸው።
በኣሁኑ ጊዜ ግዕዝ በዩኒኮድ ዕውቅና ያገኙትን የቢለን፣ ቤንች፣ ምኢን፣ ሙርሲ፣ ሱሪ፣ ትግረ፣ ትግርኛ፣ ኣገው፣ ኣውንጂ፣ ኦሮሚፋ፣ ዓማርኛ፣ ዲዚ፣ ዳውሮ፣ ጉሙዝ፣ ጉራጌ፣ ጋሞ ጎፋ እና ግዕዝ ቋንቋዎች የሚጋሯቸውን ቀለሞችና ሌሎች ያጠቃልላል። በፊደሉ ከሚጠቀሙ ቋንቋዎች መካከል ሓረሪ ኣንዱ ነው። መጽሓፍ ቅዱስ ሙሉዉን ወይም በከፊል ከ፲፭፻፮ ዓ.ም. ጀምሮ በግዕዝ ቀለሞች በማተሚያ ቤቶች ከታተሙባቸው ቋንቋዎች መካከል ሃዲያ፣ ሲዳሞ፣ ከምባታ፣ ኦሮሞ፣ ወላይታ እና ጌዴኦ ይገኙበታል።
በእጅ ጽሑፍና ማተሚያ ቤቶች ብቻ ይቀርብ የነበረው የግዕዝ ፊደል በ፲፱፻፹ ገደማ ኮምፕዩተራይዝድ ስለሆነ ኣጠቃቀሙ ወደ ኮምፕዩተር ዞሯል። ከእዚያም ወዲህ ፊደሉ የዩኒኮድ የዓለም ፊደላት መደብ ውስጥ ስለገባ እያንዳንዱ ቀለም የእራሱ ስፍራ ኣለው። ይህ የኣማርኛ ዊኪፔድያ ድረገጽም የቀረበው በእዚሁ ፊደል ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህም ፊደሉን በእጅ ስልክ መጠቀም ተችሏል። ለፊደሉ ኣጠቃቀም ኣስፈላጊ ሆነው የተፈጠሩ ኣዳዲስ የቴክኖሎጂ ዘዴዎችም የዩናይትድ እስቴትስ የባለቤትነት መታወቂያ ወይንም ፓተንት ማግኘት ጀምረዋል።
|
0 comentários:
አስተያየት ይለጥፉ